ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ በረከት የክስ ወንጀል ምስክሮች የሰጡትን ቃል አጠቃሎ በማዳማጥ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ያዘ

253

ባህር ዳር ኢዜአ ሐምሌ 5 ቀን 2011 የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ በረከት ስምኦና አቶ ታደሰ ካሳ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ምስክሮች የሰጡትን ቃል አጠቃሎ በማዳማጥ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ያዘ።

ፍርድ ቤቱ አቃቢ ህግ ያቀረባቸውን የምስክሮች ቃል  ተቀብሎ  ማጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ የመጨረሻው ምስክር የሰጡት ቃል ወደ ፅሁፍ ተገልብጦ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ  እስካሁን ምስክሮቹ የሰጡትን ቃል አጠቃሎ በማዳመጥ  ውሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።