በአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋልና ናይጀሪያ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፉ

96

ኢዜአ ሀምሌ 4/2011በግብፅ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2019 የአፍርካ ዋንጫ ትናንት ምሽት ሁለት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተደርገዋል።

ናይጀሪያ ደቡብ አፍሪካን በገጠመችበት ጨዋታ በሳሙኤል ቹኩዌዜ እና ትሩስት ኤኮንግ ግቦች 2 ለ 1 ስታሸንፍ ሴኔጋል ቤኒንን በኢድሪሳ ጉዬ ግብ 1 ለ 0 ረትታለች።

የደቡብ አፍሪካን ከሽንፈት ያላዳነች ግብ ቦንጋኒ ዙንጉ ከመረብ አዋህዷል።

ይህን ተከትሎም ናይጀሪያና ሴኔጋል ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፈዋል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ