በአጋጣሚ ሳንቲም የዋጠችው ሴት ለ12 ዓመታት ድምጿን አጣች

297

ሃምሌ 3/2011ስሟ ማሪ ማክክሬዲ ትባላለች በወቅቱም የ13 ዓመት ልጅ ስትሆን ጉዳዩን የሚከታተሉት ዶክተሮች ልጅቷን ያስቸገራት አስጨናቂ የጉሮሮ ቫይረስ ሊሆን እንደሚችል አስበው ነበር ይላል ኦዲቲ ሴንተራል፡፡

ከ12 ዓመታት በኋላ በድንገት ድምጿን የቀየረችባት  በድንገት የዋጠቻት አሮጌ ሳንቲም በጉሮሮዋ በመቀርቀሯ ምክኒያት እንደሆነ ባወቀች ሰዓት ድንጋጤ ይነበብባት ነበር ሲልም በዘገባው ሰፍሯል፡፡

ይህ በማክክሬዲ ላይ ያለፈ ታሪክ በህይወት አጋጣሚ አንዴ ሊከሰት የሚችል በመሆኑ የብዙዎችን ቀልብ ሊስብ ችሏል ያለው ዘገባው ከ12 ዓመታት በፊት በአንዲት ትንሽ አሮጌ ሳንቲም የተነጠቀችውን ደምጿን  ማግኘት መቻሏን ‘ዘ ቮይስለስ’ በሚል ርዕስ ባሳተመችው መፅሃፍ ላይ ልትከትበው መቻሏን ጠቁሟል።

በማክክሬዲ በ1972 እኤአ የ13 ዓመት ልጅ እያለች ለመጨረሻ ጊዜ በድንገት ድምጿን ያጣች ሲሆን ዶክተሮቿ የመተንፈሻ አካል በሽታ ይዟት ሊሆን እንደሚችል ገምተው እንደነበር ዘገባው አመልክቷል፡፡

ለልጅቷ ይበጃሉ የተባሉ ሁሉንም ዓይት ሙከራዎች ማድረግ ብትችልም ምንም መፍትሄ ባለመገኘቱ በወቅቱ የ13 ዓመት ልጅ የነበረችው ማክ ክሬዲ ወደ መደበኛ የትምህርት ገበታዋ በመመለስ ህይወቷን በዝምታ ለመቀጠል ተገዳለች ሲል ዘገባው ሁኔታውን ወደ ኋላ ተመልሶ ያስቃኘናል፡፡

በወቅቱ ከሁኔታው ባለቤት እስከ ቤተሰብ ድረስ ፍርሃት፣ ግራ መጋባት በመንገሱ ነገሮችን እንዴት አምኖ መቀበል እንደሚቻልም እንኳን በቅጡ የሚያውቁት ነገር እንደሌለም በዘገባው ሰፍሯል፡፡

ማክከሬዲና ጓደኞቿ በጋራ በመሆን መግባቢያ ሊሆኑ የሚችሉላቸውን ነገሮች በመፈለግ ድምፅ አልባ ህይወቷ ለማገዝም ጭምር በማሰብ የእርስ በርስ መግባቢያ ማስታወሻዎችን በማዘጋጀት  ይፃፃፉ እንደነበርም ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ይባስ ብሎ ጊዜው እየገፋ ሲሄድ ነገሮች አስቸጋሪ እየሆኑ ቢሄዱም ከመምህራኖቿ የምታገኘው ምላሽ ብርታትን ይሰጣት እንደነበር ዘገባው ያመለክታል፡፡

ከሚያደርጉላት እገዛ ከሌሎች ልጆች ጋር ሲነፃፀር  ምንም ዓይነት የተለወጠ ነገር እንደሌለ እንድታስብ  እንዳስቻላት ዘገባው ያሳያል፡፡

ዘገባው አክሎም የሷ ታሪክ በ1984 የሚጀምር ከዜናም በላይ የሆነ ጉዳይ ሲሆን ከልጅቷ ታሪክ የሚማሩ በርካታ ሰዎች ግን የሁኔታውን ክብደት በማሰብ  የኤክስ ራይ አገልግሎት አላገኘችም ነው ወይስ ሁኔታውን እንዴት አላወቁትም ነበር? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

አንደኛው ነገርም ሲታይም ዶክተሮቹ በጉሮሮዋ የተጣበቀውን ነገር ለማየት የተቸገሩ ቢሆንም ማክከሬዲን ድምጿን ያሳጣቻትን ያችን አስቸጋሪ ነገር ለማወቅ የኤክስ ራይ አገልግሎት አግኝታ እንደነበርም ዘገባው አስታውሷል፡፡

በወቅቱም በጉሮሮ ውስጥ በአግድም የተቀረቀረችውን ሳንቲም ለማየት አዳጋች እንደነበርም በዘገባው ሰፍሯል፡፡

እርስዎ ግን በጉሮሮ የተጣበቀች ሳንቲም እንዴት ድምጿን አገደች ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ? ሲልም መረጃው ይጠይቃል፡፡

ጥሩ እስካሁን ድረስም ቢሆን ልጅቷ ሳንቲሟን እንዴት እንደዋጠችው ሚስጥር ሆኖ ቆይቷል ሲልም ዘገባው ያክላል፡፡

ልጅቷ ልታስብ የምትችለው ብቸኛ ነገር ንፁህ ለስላሳ መጠጥ እንደወሰደችና በዚያ አጋጣሚም ባለመገንዘብ ሳንቲሟን እንደዋጠች ሊሆን እንደሚችልም ዘገባው ግምቱን አስቀምጧል፡፡

ነገር ግን ይህ  ያልተለመደ ታሪክ ለ12 ተከታታይ ዓመታት በጉሮሮዋ ውስጥ ተጣብቃ የቆየችው ሳንቲም ድምጿን ነጥቃት እንደቆየች ዘገባው አመልክቷል፡፡

የተለያየ ህክምና ካገኘች በኋላ ካጋጠማት የድምፅ አልባ የህይወት ጉዞ  እያገገመች ቢሆንም እስካሁን ድረስ መናገር እንደማትችል ኦዲቲ ሴንትራል በዘገባው አመልክቷል፡፡