በቀጣዮቹ አስርት አመታት የምግብ ዋጋ ሊቀንስ እንደሚችል የመንግስታቱ ድርጅት ትንበያ አረጋገጠ

131
ኢዜአ ሀምሌ 3/2011የዩ ፒ አይ ዘገባ እንደጠቆመው በቀጣዮቹ አስር አመታት ምንም እንኳ የህዝብ ቁጥር መጨመሩ ቢቀጥልም በርካታ የግብርና ምርት አይነቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ ሊኖር እንደሚችል የመንግስታቱ ድርጅት ተንብይዋል። የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በቀጣይ አስርት አመታት ውስጥ የምግብ ፍላጎት መጠን በ15 በመቶ ሊያድግ እንደሚችል ቢገመትም የግብርና ምርቶች ግን በላቀ ፍጥነት ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።
በምርትና ምርታማነት መሻሻል ሳቢያ የምርት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር፣ በተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ መታገዝ የምርት መጠኑ ሊጨምር እንዲችል ከሚያደርጉ ምክንያቶች በዋነኝነት በዘገባው ተጠቅሷል። መረጃው የገቢ መጠናቸው አነስተኛ ለሆኑ ዜጎች እንደ መልካም ዜና ሊቆጠር እንደሚችል የዘገበው ዩ ፒ አይ ቁጥራቸው በዛ ላሉ የአንዳንድ ሀገራት አርሶ አደሮች አስርተ አመታቱ ፈታኝ ሊሆንባቸው እንደሚችል አስቀምጧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም