ቻይና በኢትዮጵያ ረዥሙን ድልድይ ልትገነባ ነው

54
ሐምሌ 3/2011 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ 49 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተያዘለት ረዥም ድልድይ ልትገነባ መሆኗን ፌስ ቱ ፌስ አፍሪካ በድረገፁ አስነበበ፡፡ ግንባታውም በቻይናው ሲሲሲሲ ኮንስትራክሽን ኩባንያ የሚከናወን ሲሆን ኩባንያው የድልድዩን ግንባታና ዲዛይን በሚመለከት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የስምምነት ፊርማ ማስቀመጣቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡ በባህርዳር አካባቢ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ድልድይ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ዕቅድ ተይዞለታል፡፡ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ድልድይ 21.5 ሜትር ስፋትና ሶስት መስመሮችን የሚይዝ ሲሆን ይህም የብስክሌት፣ የመኪና መስተላለፊያና የእግረኛ መንገድን የሚያካትት እንደሆነ በዘገባው ሰፍሯል፡፡ የፕሮጀክቱ ወጪ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ስለመሆኑም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ የባህርዳሩ አባይ ድልድይ ከተጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ እረዥሙ ድልድይ እንደሚሆን የታወቀ ሲሆን ጥቅምት ወር 2006 ለትራፊክ ክፍት የሆነውን 319 ሜትር ርዝመት ያለውን የባሽሎ ወንዝ ድልድይ በርዝመት እንደሚበልጥ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የቻናው ኮንስትራክሽን ኩባንያ ሲሲሲሲ በሃገሪቱ የሚገነቡ የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የሚያከናውን ሲሆን  በዚህም የኮምቦልቻን ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በሃገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የአዲስ-አዳማ ፈጣን መንገድ፣ ቦሌ አካባቢ የሚገኘውን የአፍሪካ ጎዳና መንገድ፣ የመኢሶ-ጅቡቲ ባቡር መንገድ ብሎም በአዲስ አበባ የቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ ማስፋፊያ ግንባታዎችን እያከናወነ የሚገኝ ተላቅ ተቋም መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ቢሆን ኩባንያው አራት በሂደት ላይ ያሉ ታላላቅ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክችን እያከናውነ ሲሆን ከናዛ ውስጥ የሃዋሳን አየር መንገድን ከጥቁር ውሃ/ቢሻን ጉራቻ/ የሚያገናኝ መንገድግንባታ፣ ከጅግጅግጋ ገለሽ ያለ መንገድ ግንባታን፣ ከጨረርቲ ሃገር መኮር መንገድ ግናባታና አርሲ ነገሌ ሃዋሳ መንግድ ግንባታን እያከናወነ የሚገኝ ፕሮጀክት መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም