ሆንግ ኮንግ ወንጀለኞችን ለቻይና አሳልፎ የሚሰጠውን የህግ ረቂቅ ሊትሰርዝ ነው

57
ሐምሌ 2/2011 ሆንግ ኮንግ እ.አ.አ በ2020 ወንወጀለኞችን ለቻይና አሳልፎ የሚሰጠውን የህግ ረቂቅ እንደምትሰርዝ የግዛቲቷ ፕሬዘዳንት ካሪይ ላም ገለፁ። ፕሬዘዳንቷ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቀጣይ መንግስታቸው ይህን  የህግ ረቂቅ ሙሉ በሙሉ ከአገራቸው የህግ ማዕቀፍ ለመሰረዝ ጠንክሮ ይሰራል ብለዋል ። ነገር ግን ላም ተቃውሞ ሰልፈኞች  ሙሉ በሙሉ ከቻይና ለመነጠል ያሳዩትን ፍላጎት አስመልክቶ  አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ይህን  የህግ ረቂቁ ተከትሎ በግዛቲቷ ለበርካታ ሳምንታት ሲካሄዱ የቆዩ ሲሆን በዚህ ምክኒያት ህጉ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱ ይታወሳል። "ይሁን እንጂ መንግስት ለተግባራዊነቱ ያለው ቁርጠኝነት በህዝቡ ዘንድ አልፎ አልፎም ቢሆን ጥርጣሬዎችን መፍጠሩን ካሪይ ላም ጠቁመዋል። ይህን አስመልክቶ ላም  በተደጋጋሚ  ሲናገሩ “ከዚህ በኋላ ወደ ኋል የሚመለስ  እቅድ አይኖርም፣  የህግ ረቂቁ ጉዳይ አስቀድሞ ሞቷል” ብለዋል። ባለፈው ጊዜ ፕሬዘዳንት ላም  በፈረንጆች 2020 የዚህ የህግ ረቂቅ ግብዓተ መሬት መፈሚያ ይሆናል ማለታቸው ታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም