የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል አሉ

77
ባህር ዳር ሰኔ 29/2011 የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መንግስት የመሪነቱን ሚና፤ ህብረተሰቡ ደግሞ የአጋዥነት ድርሻቸውን እንዲወጡ በባህር ዳር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ምክረ ሃሳብ ለገሱ ። በባህር ዳር ከተማ የጣና ክፍለ ከተማ ነዋሪና የሀገር ሽማግሌ አቶ ሰውነት ተገኘ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት መንግስት ለሀገሪቱ ሰላም መረጋገጥና ለህግ የበላይነት መከበር ትልቁን ድርሻ ሊወስድ ይገባል። አሁን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየታየ ያለውን የሰላም መደፍረስ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት በተዋረድ ያለውን መዋቅር ፈትሾ ማስተካከልና ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ዋስትና መስጠት እንዳለበት የሀገር ሽማግሌው ተናግረዋል ። "ከዘላቂ ሰላም ዋነኛው ተጠቃሚ የሆነው ህብረተሰቡም መንግስት የህግ የበላይነት ለማስከበር የሚያደርገውን ጥረት ሊደግፍ ይገባል" ብለዋል ። የህግ የበላይነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ሰርቶ ማደር አስቸጋሪ መሆኑን የጠቆሙት ደግሞ ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ አቶ ግርማ ሞገስ ናቸው። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት ከመጠላለፍና መገዳደል በመውጣት በመነጋገር፣ በመደማመጥና በመግባባት ሰላምን ማረጋገጥ ይቻላል በሚል ያሳየውን ትእግስት በመጠኑም ቢሆን የህግ የበላይነነት እንዲላላ አድርጎታል የሚል ሃሳብ እንዳላቸው ገልፀዋል ። "በተፈጠረው ክፍተት በጠራራ ፀሐይ መሪዎቻችን እንድናጣ አድርጎናል" ያሉት የሀገር ሽማግሌው፣ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ማስፈን ይዋል ይደር የሚባል አለመሆኑን አስረድተዋል ። "ሰላም ከምንም በላይ አስፈላጊ በመሆኑ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የህይወት መስዋትነት ጭምር በመክፈል ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ግንባር ቀደም ተዋናዮች መሆን አለብን" ሲሉም ገልጸዋል ። እንደ አቶ ግርማ ገለጻ መንግስትህግየሚተላለፉአካላትንስርዓትበማስያዝየዜጎቹንዋስትናየመጠበቅግዴታውንበብቃትመወጣት ይኖርበታል። የሀገር ሽማግሌዎች ለህግ የበላይነት መከበርና ለሰላም መረጋገጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ምቹ ሁኔታ ሊመቻችላቸው እንደሚገባም አቶ ግርማ ተናግረዋል ። የአማራ ሴቶች ማህበር ዋና ፀሐፊ ወይዘሮ አዲስ ጫኔ በበኩላቸው እንዳሉት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ከዚህ በፊት የተሰሩት የግንዛቤ ማጎልበቻ ስራዎች አናሳ መሆናቸው የሚፈለገውን ሰላም ማረጋገጥ አልተቻለም ። የህግ የበላይነት ካልተረጋገጠ በግንባር ቀደምነት ሴቶች የችግሩ ተጠቂዎች እንደሚሆኑ የገለፁት ወይዘሮ አዲስ፣ "ማህበሩ በቀጣይነት አባላቱ የሰላም አምባሳደር ሆነው እንዲሰሩ ግንዛቤ የማሳደግ ሥራ ይከናወናል" ብለዋል ። የአማራ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት ኃይለሚካኤል ካሳሁን በበኩሉ በክልሉ ስድስት ሚሊዮን ወጣቶች ቢኖሩም  በህግ የበላይነት ላይ የግንዛቤ ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገው ጥረት አናሳ መሆኑን አስረድቷል ። በአካባቢያቸው የሰላም መደፍረስ ችግር ሲከሰት ራሳቸውን በበጎ ፈቃድ ሥራ አደራጅተው የአካባቢውን ሰላምና መረጋጋት በመጠበቅ አርያነት ያለው ተግባር የሚፈፅሙ ውጣቶች መኖራቸውን የጠቀሰው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ይህንኑ በማስፋት ለህግ የበላይነት መከበር የበኩላቸውን እንደሚወጡ አመልክቷል። "መንግስትም የወጣቱን ችግር በመፈተሽ ሰፋፊ የሥራ እድሎች በመፍጠር ተጠቃሚነታችንን ሊያረጋግጥልን ይገባል" ሲልም ወጣት ኃይለሚካኤል ተናግሯል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም