ሕወሓት አስቸኳይ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

88
መቀሌ ሰኔ 3/2010 የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/  አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ በመቀሌ ከተማ  የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ተጀመረ። በዝግ የተጀመረው አስቸኳይ ጉባኤ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ  ድርጅቱ  ትናንት ማምሻውን  ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው ጽሁፍ ገለልጿል። ኢትዮ - ኤርትራን አስመልክቶ ኢህአዴግ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ድርጅቱ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው የሁለቱንም ሀገራት ህዝቦች ዘላቂ ጥቅምና አንድነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል። ሕወሓት ትክክለኛ ባልሆኑ  ወሬዎች ህዝቡ እንዳይደናገር ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ጉዳዩን በዝርዝር ከአባላቱና ከህዝቡ ጋር እንደሚወያይበትም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም