የሱዳን ወታደራዊ ሃይል እና ተቃዋሚዎች ስልጣን ለመጋራት ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
የሱዳን ወታደራዊ ሃይል እና ተቃዋሚዎች ስልጣን ለመጋራት ተስማሙ
59
ሰኔ 28 /2011 የሱዳን ወታደራዊ ሃይል አመራሮች በአገሪቷ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ስልጣን በመጋራት አብረው ለመስራት መስማማታቸውን አደራዳሪዎቹ ገለፁ፡፡ ሁለቱ አካላት ቢያንስ ለሶስት አመታት በጋራ እንደሚሰሩ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ ህብረት እንደገለፀው በሀገሪቱ በቅርቡ የተከሰተውን ግጭት የሚመረምር ገለልተኛ አካል ለማቋቋምቃል ገብተዋል፡፡ ሱዳናውያን የስምምነቱን ዜና እንደሰሙ አደባባይ በመውጣት ደስታቸው ገልፀዋል ተብሏል፡፡ ሱዳን በሚያዝያ ወር ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ስልጣን መልቀቅን ተከትሎ መረጋጋት ርቋት መቆየቷ ተገልጿል፡፡ የቀድሞ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር እኤአ በ1989 በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡ ምንጭ፡-ቢቢሲ