አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቀረቡ

243

ሰኔ 27/2011 በሩሲያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን የተሾሙት አለማየሁ ተገኑ ትናንት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቅርበዋል።
አምባሳደር አለማየሁ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር በቆይታቸው በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነትና ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ከ120 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው በማለት መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

በማያያዝም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የጠበቀ የሁለትዮሽ፣ ክልላዊና ዓለም አቀፍ ትብብር አጠናክሮ ለማስቀጠል ሩሲያ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

አምባሰደሩ በሩሲያ ቆይታቸው አስፈላጊው ድጋፍ እንደማይለያቸውም ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገልፀዋል።