የኩንሻን ከተማ በድሬዳዋ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ዘመናዊ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልትገነባ ነው

81
ድሬዳዋ ሰኔ 26 / 2011የቻይናዋ ኩንሻን ከተማ በድሬዳዋ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ዘመናዊ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ከንቲባው አስታወቁ። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተማዋን የኢንዱስትሪ ማዕከል እያደረጓት ነው ብለዋል፡፡ በከንቲባ ዙ ዩ ዶንግ የተመራ የመንግሥትና የባለሃብቶች ቡድን ትናንት በከተማዋ ጉብኝት ካደረገ በኋላ እንደተናገሩት ከተማቸው የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪውን ለመመስረት ዝግጅቷን አጠናቃለች። ግንባታው በሁለት ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቀው ፓርክ ለበርካታ ወገኖች ሥራ እንደሚፈጥር አስረድተዋል። ፓርኩ አገራቸው ከኢትዮጵያጋር ያላት ሁለንተናዊ ግንኙነት ማሳያ መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል፡፡ አገራቸው በዘርፉ ያላትን ልምድ በማካፈል የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍ እንደምታደርግም አስታውቀዋል፡፡ በዚህም በድሬዳዋ በገነቡት የማሰልጠኛ ተቋማቸው ከሁሉም የአገሪቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለተውጣጡ 30 ባለሙያዎች በፓርኮች አስተዳደርና አሰራር የ10 ቀናት ሥልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሃር የቻይና ሞዴል የኢንዱስትሪ ግዛት የሆነችው ከተማ ፓርኩን ለመገንባት የምታደርገው እንቅስቃሴ ለማሳካት እገዛ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከተማዋ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና የወጣቶች የክህሎት ማሰልጠኛ ተቋም በመገንባት እንድትደግፍ ጠይቀዋል፡፡ በመንግሥትና በግል ዘርፍ የሚገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተማዋን በአጭር ጊዜ የምስራቁ የአገሪቱ ክፍል የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከልነቷን እንደሚያረጋግጡ አቶ ከድር እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ለሊሴ ነሜ በቻይና የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ሞዴሏ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷ ከሥራ ዕድል ፈጠራ በተጨማሪ የኢንዱስትሪ -የዩኒቨርሲቲ ትስስር ለማጠናከርና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚያጎለብት አስታውቀዋል፡፡ ከንቲባውና የልዑካን ቡድን የአገራቸው ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋለ ነዋያቸውን በማፍሰስ የአገሪቱን ኢንዱስትሪ ልማት እንዲያግዙ ጠይቀዋል፡፡ ሁለቱከተሞችበነሐሴወርየእህትማማችነትስምምነትይፈራረማሉተብሎይጠበቃል፡፡ ኩንሻንበደቡብ ምስራቅቻይናበጂያንግሱግዛትየምትገኝናየኢንዱስትሪፓርኮችከተማናት፡፡ የዓለም አንድ ሶስተኛ ላፕ ቶፖችና 50 በመቶ ለአለም ገበያ የሚቀርበውን የእጅ ስልክ (ሞባይል) ምርት የምታመርት የኢንዱስትሪ ከተማ መሆኗም ተገልጿል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም