በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የተመዘገበው ውጤት የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አልፈታም ...ሚኒስቴሩ

99
ሀዋሳ ሰኔ 25/2011 በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የተመዘገበው ውጤት የከተማውን ህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንዳልፈታ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አቅርቦት ማሻሻያ እንዲሁም ሰነድ አልባና ህገወጥ የመሬት ይዞታዎችን ስርዓት ማስያዝ ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ በሃዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ካሊድ አብዱራህማን በእዚህ ወቅት እንዳሉት በማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች፣ በሰነድ አልባና ህገወጥ የመሬት ይዞታዎች፣ በጽዳትና አረንጓዴ ልማት ላይ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል። በተሰሩ ሥራዎች የተገኙ ውጤቶች ከክልል ክልልና ከከተማ ከተማ ልዩነት ቢኖራቸውም የከተማውን ህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በበቂ ሁኔታ አልፈቱም ብለዋል። ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት ከተሞች በፕላን አለመመራታቸው የሕብረተሰቡን ፍላጎት ታሳቢ ያደረጉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተግባራት በአግባቡ እንዳይከናወኑ አድርጓል። ይህምህገወጥግንባታእንዲስፋፋምክንያትመሆኑንጠቁመውየሰነድአልባይዞታዎችእየተበራከተመምጣትከተሞችእንዳያድጉምክንያትመሆኑንተናግረዋል፡፡ “የከተማአመራሩየመሬትሃብቱንበአግባቡአለማወቁናአለመምራቱአንዱየችግሩምንጭነው”ያሉትሚኒስትርዲኤታውየንቅናቄመድረኩምይህንንችግርለመፍታትታስቦመዘጋጀቱንነውየጠቆሙት። ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የለውጥ ሥራ መጀመሩን ገልጸውለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ ስራውህብረተሰቡንባሳተፈመልኩመከናወንእንዳለበትጠቁመውሚኒስትርመስሪያቤቱክልሎችንእንደሚደግፍምገልጸዋል፡፡ በሚኒስቴሩ የመሬት ልማትና ማናጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብዙአለም አድማሱ በበኩላቸው  “በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ጠንካራ የመሬት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ 23 ከተሞች የተጀመረው የካዳስተር ሥራ ችግሩን በመፍታት ስራውን ውጤታማ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡ የከተሞችን አስተዳደር ወሰን በአግባቡ ከመለካት በተጨማሪ ህጋዊ፣ ሰነድ አልባና ህገወጥ ይዞታዎችን መለየትም ተገቢ መሆኑን ነው የገለጹት የኦሮሚያ ክልል ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ዶክተር ጋረደው ድንቁ በክልሉ 600 የሚጠጉ ከተሞች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ዙሪያ ባሉ የክልሉ ከተሞች ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩንም አመልክተዋል፡፡ ዶክተር ጋረደው እንዳሉት ችግሩን ለመከላከል የተሰሩ ሥራዎች ቢኖሩም ውጤታማ መሆን አልቻሉም። ህገወጥግንባታዎችንለማፍረስየሚደረግእንቅስቃሴንከወቅታዊየፖለቲካሁኔታጋርለማያያዝጥረትየሚደረግበትአጋጣሚመኖሩንምጠቁመዋል፡፡ “በህገ ወጥ መንገድ ለተያዙ መሬቶች በቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥና ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ለመከላከል ህግ ማስከበር ላይ የተጠናከረ ስራ እንሰራለን” ብለዋል። በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሸምሰዲን ሃሰን በበኩላቸው እንዳሉት በመሬት ዘርፍ የሚስተዋለውን ህገወጥነት ለመከላከል የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ እየተሰራ ነው፡፡ ችግሩን ለመካለከል በሚደረግ ሂደት ተደራጅተው ጥያቄ የመጠየቅ ልምድ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “በመሬት ዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የካሳ ክፍያና የሊዝ ስርዓቱ የአርሶ አደሩን ጥያቄ በሚፈታ መልኩ መስተካከል ይኖርበታል” ሲሉም ገልጸዋል። በመድረኩ ከደቡብ፣ ከኦሮሚያና ከጋምቤላ ክልል አመራሮችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን በቀረቡ ሰነዶች ላይም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም