ሃረር የሚገኘው የገበያ ማዕከል የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት

144
ሰኔ 25/2011 በሃረር ከተማ የሚገኘውና በተለምዶ መብራት ኃይል የገበያ ማዕከል እየተባለ የሚጠራው ስፍራ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት ቀጠሎ ተነስቶበታል። የኢዜአ ሪፖርተር ከስፍራው እንደገለጸው ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት ከግማሽ ሰዓት በፊት የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በአካባቢው የሚገኙትን የንግድ ሱቆች እያወደመ  ይገኛል። በአሁኑ ሰዓትም የክልሉና የፌዴራል ፖሊስ፣የመከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው ነዋሪዎች እሳቱ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከልና ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ። የንግድ ቤቶቹ ባለቤቶችና የከተማው ነዋሪዎችም አንዳንድ ንብረቶችን ከቃጠሎው  ለማትረፍ እየሞከሩ መሆናቸውንና ግርግሩን ተከትሎም ዝርፊያ እንዳይካሔድ ፖሊስ እየጠበቀ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ተችሏል። በአደጋው የደረሰውን የጉዳት መጠንና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም