በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሰብል ላይ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋን ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው

120
ሰኔ 22/2011 በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በ8 ሺህ ሄክታር የበቆሎና ማሽላ ቡቃያ ላይ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ገለቱ ሊኢዜአ እንደገለጹት በዘኑ ከሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የአንበጣ መንጋው ተከስቷል ። መንጋው ከበቆሎና ማሽላ ሰብሎች በተጨማሪ በግጦሽ ሳርና ቅጠላ ቅጠሎች ላይ  መከሰቱንም ተናግረዋል ። የአንበጣውን በዘመናዊና በባህላዊ ዘዴ የመቆጣጠር ሥራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል ። ከክልልና ከፌደራል የቀረበ ከ2ሺህ ሊትር በላይ ፀረ ተባይ ኬሚካል ርጭት መጀመሩንም ጠቅሰዋል ። መንጋው ወደ ሌሎች አካባቢ እንዳይስፋፋ አርሶ አደሩ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ የመከላከል ሰራ አየተካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል ። በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ የጃራ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አህመድ ያሲን በበኩላቸው በግማሽ ሄክታር የማሽላ ማሳቸው ላይ አንበጣ መከሰቱን ተናግረዋል ። ከሌሎች ለርሶ አደሮች ጋር በመሆን በባህላዊ መንገድ እያደረጉ ካለው የመቆጣጠር ስራ በተጨማሪ ፀረ ተባት ኬሚካል እንዲረጭላቸው ለሚመለከተው የመንግስት አካል ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል ። በብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ በመኸር እየለማ ካለው 60 ሺህ ሄክታር መሬት 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበው ታውቋል ።፡          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም