የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት በፊፋ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመታደም ወደ ሞስኮ ያቀናሉ

49
አዲስ አበባ ሰኔ 2/2010 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በሩሲያ ሞስኮ በሚካሄደው የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመታደም ዛሬ ማምሻውን ወደ ሞስኮው ያቀናሉ። ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም በሚካሄደው 68ኛው የፊፋ ጠቅላላ ጉባኤ ለመሳተፍ ከአቶ ኢሳያስ በተጨማሪ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አወል አብዱራሂም እና ዋና ጸሐፊው አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ ወደ ስፍራው ያቀናሉ። አቶ ኢሳያስ ከፊፋ በተጨማሪ ነገና ከነገ በስቲያ በሞስኮ በሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ስብሰባ ላይ እንደሚታደሙም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ.ም በሚጀመረው የዓለም ዋንጫ የሞስኮ ሉዚኒስኪ ስታዲየም መክፈቻ ስነ-ስርዓትና አዘጋጇ ሩሲያና ሳዑዲአረቢያ በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ እንደሚታሙ ነው አቶ ሰለሞን የጠቆሙት።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም