የጀነራል ሰዓረ መኮንን እና የሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የቀብር ሥነስርአት ተፈጸመ

112
መቀሌ ሰኔ 19/2011የኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና የሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የቀብር ሥነስርአት መቀሌ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተፈጸመ። በቀብር ስነስርአቱ ላይም ለክብራቸው 17 ጊዜ መድፍ ወደሰማይ ተተኩሷል። በሟቾቹ መቃብር ላይ የክልሉ ርዕስ መስተዳድር፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተወካዮችና የተለያዩ አካላት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። ለጀነራል ሰዓረ መኮንን እና ለሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ በትግራይ የሰማዕታት ኃውልት ሽኝትና ሃይማኖታዊ የጸሎት ስነስርአት ከተከናወነ በኋላ በመከላከያ ሠራዊትና በክልሉፖሊስ ማርሽ ባንድ በመታጀብ የቀብር ሥነስርአታቸው ዛሬ ከቀኑ 9፡30 ላይ ተፈጽሟል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም