በህገ-ወጥ መንገድ በሚካሄድ የግብይት ስርዓት አገሪቱ በየዓመቱ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ታጣለች

74
ሰኔ18/2011 በኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በሚካሄደው የግብይት ስርዓት አገሪቱ በየዓመቱ አስከ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር የሚደርስ ገቢ እያጣች መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።  በዓለም ታዋቂ ከሆነው የምጣኔ ኃብታዊ መፅሄት -ኢኮኖሚስት  ጋር በመተባበር በተዘጋጀውናበአህጉራዊ የንግድ እንቅስቃሴ ችግሮች፣ መንስኤዎቻቸውና መፍተሄዎቹ ዙሪያ የመከረ ጉባኤ በአዲስአበባ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ላለፉት አምስት ዓመታት ከፖሊሲ አውጪው አካላትና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር  የጉምሩክ  ኮሚሽን  ያካሄደው  ጥናት  ቀርቧል።   በጥናቱ እንደተመለከተው በኢትዮጵያ ከሚካሄደው  አጠቃላይ  የአገር  ውስጥ ግብይት ስርዓት ውስጥ40 በመቶ ያህሉ በህገ-ወጥ መንገድ በሚገቡ ምርቶች የተያዘ ነው።   በዚህም አገሪቱ ከግብይቱ ስርዓቱ ማግኘት የነበረባትን ዘጠኝ ቢሊዮን ብር  በየዓመቱ ታጣለች፣ ይህገቢ 72  ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር አገራዊ  ኢኮኖሚውን በከፍተኛ መጠን ያግዝ ነበርተብሏል። እንደጥናትሪፖርቱ 45  በመቶ የትንባሆ ምርቶች፣   48 በመቶ  የጨርቃ  ጨርቅ   ምርቶች እንዲሁም 30 በመቶመድሃኒት  በህገ-ወጥ  መንገድ  ወደአገር ውስጥ በመግባት ገበያውን የሚያውኩትቀዳሚዎቹ ሸቀጦች ናቸው። በዚሁ ህገ ወጥ የግብይት ስርዓት አማካኝነት ወደአገር የሚገቡ  ጊዜ  ያለፈባቸው መድሃኒቶችምየህብረተሰቡን ጤና ስጋት ላይ የሚጥሉ መሆናቸውንም ጥናቱ አመልክቷል። የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀባትእንደተናገሩት በአገሪቱ ድንበር አካባቢዎች የሚገኝማህበረሰብ አኗኗሩ ከኮንትሮባንድ ገቢ ጋር የተያያዘ በመሆኑ በፌደራል ፖሊስና ጉምሩክ አማካኝነትመቆጣጠር ባለመቻሉ በየጊዜው በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ቁሳቁስ ይገባል፤ ይወጣል ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ፈንታ ማንደፍሮበበኩላቸው መንግስት በድንበር አካባቢዎች ያለውን ህገ ወጥ ንግድ ለማስቆም በቅድሚያአማራጮችን ማሰብ አለበት ብለዋል። ችግሩን ለመቅረፍም መንግስት የጎረቤት አገሮችን የግብር ስርዓት በማጤን የግብር በአገሪቱ ስርዓት ላይ ማስተካከያ በማድረግና ለጠረፍ ነዋሪዎቹም የተሻለ መተዳደሪያ መዘየድ እንዳለበት ተባባሪፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አያይዘውም መንግስት የግብር ማሰተካከያዎችን ሲያደርግ ህጋዊ ነጋዴዎችንያበረታታል፤ ህገ-ወጦችን ደግሞ ወደህጋዊ ለማምጣት መልካም አጋጠሚ ይፈጥራል ነው ያሉት።   
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም