የአገር ሽማግሌዎች መማክርት ጉባኤ ዜጎች በጋራ እንዲቆሙ ጠየቁ

65
ሰኔ 17/2011 በአገሪቷ አሁን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ዜጎች በጋራ እንዲቆሙ የአገር ሽማግሌዎች መማክርት ጉባኤ አሳሰቡ። ችግሩን በብልሃትና በአርቆ አሳቢነት  የእርስ በእርስ ግንኙነትና ህብረትን በማጠናከር  የአገሪቷን ሰላም ማስጠበቅ  ተገቢ መሆኑንምመልእክታቸው አስተላልፈዋል። የጉባኤው አባላት  በአማራ ክልል በተፈፀመው እኩይ ተግባር ህይወታቸውን ላጡ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ዶክተር አምባቸው መኮንንና የአደረጃጀትአማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ  የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር  ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ህልፈተ  ህይወትም ጉባኤውየተሰማውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ ድርጊቱን በጽኑ አውግዘውታል። በዚህም ህዝቡ በተፈጠረው ድርጊት ከስሜታዊነት በመውጣት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር በጋራ እንዲቆሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም ከመንግስት ጎን በመሆን ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡና አስፈላጊው  እርምጃ እንዲወሰድባቸው  ህዝቡ የበኩሉንሊወጣ እንደሚገባው አሳስበዋል። ድርጊቱ ፈጽሞ ከኢትዮያዊነት ስብእና እና ባህል ያፈነገጠ ነው ያሉት የጉባኤው  አባላት  መንግስት ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመፍታት  ከምንግዜውም  በላይ  ቁርጠኝነቱን  ማሳየት  አለበትም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም