ተቋማት በተሰው የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ ነው

60
ሰኔ 16/2011 የተለያዩ ተቋማት በአማራ ክልልና በመከላከያ ከፍተኛ አመራር ላይ በደረሰው የህይወት መስዋዕትነት የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ነው። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንንና የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እንደዚሁም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንንና የአገልግሎ ዘመናቸውን አጠናቀው በጡረታ የተሰናበቱት ሜጀር ጀኔራል ገዛኢ አበራ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ህይወታቸው አልፏል። በመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ በደረሰው መስዋዕትነት የተለያዩ ተቋማት የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ይገኛሉ። ከእነዚህም ውስጥ የሰላም ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስትር፣ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ)፣ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንቨሰትመንት ኮሚሽን ይገኙበታል። በአማራ ክልል ትናንት በተደረገው የመፈንቅ መንግስት ሙከራ ርዕሰ መስተዳደሩ ዶክተር አምባቸው መኮንንና የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ ተሰውተዋል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ በአማራ ክልል የተደረገውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማክሸፍ በመስራት ላይ የነበሩት ጀነራል ሰዓረ መኮንን በጠባቂያቸው ጥቃት ደርሶባቸው የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል። አብረዋቸው የነበሩት በጡረታ የተገለሉት ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። ድርጊቱ የሁሉንም ኢትዮጵያዊን ልብ የሰበረ ሲሆን የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች አውግዘውታል። የተለያዩ ተቋማትም በተሰዉት የስራ ሃላፊዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል። የተለያዩ ተቋማት በደረሰው ጥቃት የህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉት ሁሉ የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም