የበቆሎ ምርጥ ዘር ያለ ሕጋዊ ፈቃድ የሸጠ ነጋዴ በሰባት ዓመት ጽኑ እሥራትና 150ሺህ ብር ተቀጣ

115
አምቦ ሰኔ 14 /2011 በምዕራብ ሸዋ ዞን ትቤ ከተማ የበቆሎ ምርጥ ዘር ያለ ሕጋዊ ፈቃድ በሱቅ ውስጥ ሲሸጥ የተገኘ ነጋዴ በሰባት ዓመት እሥራትና 150ሺህ ብር ተቀጣ። በምዕራብ ሸዋ ዞን ትቤ ከተማ የበቆሎ ምርጥ ዘር ያለ ሕጋዊ ፈቃድ በሱቅ ውስጥና ከተመን በላይ ሲሸጥ የተገኘ ነጋዴ በሰባት ዓመት ጽኑ እሥራትና 150ሺህ ብር ተቀጣ። የባኮ ትቤ ወረዳ ፍርድ ቤት ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው ጎበና ገለቶ ላይ ቅጣቱ የተወሰነው ያለ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ምርጥ ዘር ከሌሎች ሸቀጦች ጋርና  ከተተመነለት ዋጋ አስበልጦ ሲሸጥ  በመገኘቱ ነው። ግለሰቡ ሕጋዊ ፈቃድ በሌለው ንግድ በመሰማራት ግብዓቱን መንግሥት ለአርሶ አደሩ ከሚያቀርብበት 660ብር በእጥፍ አስበልጦ በ1ሺህ300ብር ሲሸጥ መገኘቱንም የፍርድ ቤቱ ዳኛ አቶ ምስጋኑ ቦራ አስረድተዋል። ግለሰቡ ቅጣቱ የተወሰነበት ምርጥ ዘሩን ሚያዝያ 17 ቀን 2011 በሱቅ ውስጥ ሲሸጥ በማስረጃ በመረጋገጡ ነው ብለዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም