የትግራይ ንግድ ማህበረሰብ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌ ቶን ሊያዘጋጅ ነው

133
መቀሌ ሰኔ 14 / 2011  የትግራይ ንግድ ማህበረሰብ በክልሉ ልማት ተሳትፎ የሚያደርጉበት የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌ ቶን ሊያዘጋጅ መሆኑን ኮሚቴው አስታወቀ፡፡ የክልሉ ተወላጆችና የክልሉን ልማት ከሚደግፉ ኢትዮጵያውያን 250 ሚሊዮን ብር ይሰበሰባል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ የኮሚቴው አባል አቶ አሸናፊ ኃይሉ እንደገለጹት የፊታችን እሁድ የሚካሄደው ቴሌ ቶን ትምህርት ቤቶችንና መንገዶችን ለማስገንባት ይውላል። ማህበረሰቡየክልሉመንግሥትባቀረበውጥሪላይውይይትናምክክርማድረጉንአቶአሸናፊተናግረዋል። ማህበረሰቡ በቀጥታ ከሚለግሰው ገንዘብ በተጨማሪ ለሽያጭ የቀረቡ 100ሺህ በራሪ ወረቀቶችና 25ሺህ ቲ ሼርቶች ለሽያጭ መቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡ ለገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ስኬት ነጋዴዎች በአንድ ቆመናል ያሉት ደግሞ አቶ ፍጹም አስገዶም የተባሉ ሌላው የኮሚቴው አባል ናቸው፡፡ የገቢ ማሰባሰቢያ አላማ ዳስ ላይ ለሚማሩ ህጸናት የተሻለ ህንጻ ለመስራትና መንገድ የሌላቸው የገጠር ቀበሌዎችን ደግሞ በመንገድ ለማገናኘት ነው ብለዋል፡፡ በቴሌ ቶኑለመሳተፍ የቀጥታ ስርጭት ገቢ ማሰባሰቢያ 0992 84 48 23፣0992 84 48 24፣0992 84 48 25፣0992 8448 26፣0992 84 48 27 ደውለው በክልሉ ልማት አሸራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም