ሴት ሚኒስትሮች የሚካፈሉበት የእግር ኳስ ጨዋታ በመጪው እሁድ ይካሄዳል

72
አዲስ አበባ ሰኔ14/2011  ኢትዮጵያዊያን ሴት ሚኒስትሮች የሚካፈሉበት የእግር ኳስ ጨዋታ በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ሳምንት ''ኦሎምፒዝም ለሰው ልጆች ሰላም፣ ክብርና አንድነት'' በሚል መሪ ሀሳብ ከሰኔ 16 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ የኦሎምፒክ ሳምንትን በአዲስ አበባም በተለያዩ ስፖርታዊ ፕሮግራሞች ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል። የኦሎምፒክ ሳምንቱ ከሚከበርባቸው አንዱ የኢትዮጵያ ሴት ሚኒስትሮች ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህበተጨማሪየኢህዴግባለስልጣናትከተፎካካሪፓርቲመሪዎችጋርየሚያደርጉትጨዋታምበጉጉትከሚጠበቁሁነቶችመካከልነው። እንዲሁም ኮሜዲያኖች ከስፖርት ጋዜጠኞች ጋር እና የኢትዮጵያ ቡናና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ደጋፊዎችም ይጫወታሉ ተብሏል። ጨዋታዎች የሚካሄዱበት በዋናነት መሸናነፍ ላይ ትኩረት ሳያደርጉ በመሆኑ እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል። ጨዋታው በመጪው እሁድ ከአራት ሰዓት ጀምሮ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል። በኦሎምፒክ ሳምንቱ የገቢ ማሰባሰቢያ የሚውል ተግባርም የሚከናወን ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ 20 ሚሊዮን ብር ለኦሎምፒክ ኮሚቴ ገቢ ይገኛል ተብሎ ይታሰባል። የኦሎምፒክ ሳምንቱ በተለያዩ ክልሎች በስፖርታዊ ውድድሮች እንደሚከበርና በአዲስ አበባ ደግሞ ፓናል ውይይትን ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል። በዚህ የኦሎምፒክ ሳምንት ህብረተሰቡ ኮሚቴውን በገንዝብ ድጋፍ የሚያደርግበት አሰራርም የተዘረጋ በመሆኑ ህብረተሰቡ በአቅሙ ልክ ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል። ይህ የኦሎምፒክ ሳምንት ሲከበር በዋናነት የኦሎምፒክ ፍልስፍና በትክክል ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ይከናወኑበታል። በእለቱ ጠዋት ላይ የሩጫ ውድድር ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፖርትና የጽዳትና ችግኝ ተከላ ስራም በመስቀል አደባባይና አካባቢው እንደሚከናወን ተገልጿል። በሌሎቹ የሳምንቱ ቀናትም በፓናል ውይይት በሙዚቃ ዝግጅትና በሌሎችም የኦሎምፒክ ሳምንቱ ተከብሮ የሚውል ይሆናል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም