በኢትዮጵያ የገጠር መንገዶች ያሉበት ሁኔታ በየዓመቱ ጥናት ያስፈልገዋል ተባለ

108
አዲስ አበባ ሰኔ14/2011 ለክልሎች የመንገድ ጥገና ፍትሃዊ የበጀት ክፍልል እንዲኖር ለማስቻል መንገዶቹ ያሉበት ሁኔታ በየዓመቱ ጥናት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት በስድስት ክልሎች የመንገድ ሁኔታ፣ አያያዝ፣ የሙያዊና የፈንድ ድልድል አስመክልቶ ባስጠናው ጥናት ላይ ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት አካሂዷል። ጥናቱ በመቀሌ፣ ባህርዳር፣ አዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ አዳማና ጅማ ዩኒቨርስቲዎች የምህንድስና የትምህርት ክፍሎች የተደረገ ነው። በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የትራንስፖርት ዘርፍ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር አሸናፊ አረጋዊ ዩኒቨርስቲው በትራግይና አፋር ክልል ገጠር መንገዶች ላይ ያደረገውን ጥናት አቅርበዋል። ጥናቱ በተደረገባቸው አፋርና ትግራይ ክልሎች የሚገኙ ገጠር መንገዶች ከውሃ ፍሳሽና ሌሎች ችግሮች ጋር ተያይዞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጥገና ሲደረግላቸውም ደረጃውን በጠበቀና በላብራቶሪ በተፈተሸ ግብአት አለመሆኑን በጥናቱ ተለይቷል። ለዚህም እንደምክንያት የሚያነሱት መንገዶች ያሉበት ሁኔታ ቀደም ብሎ ባለመጠናቱና የሚያስፈልገው የጥገና መጠን ስለማይታወቅ ነው የሚል ሃሳብ ያነሳሉ። በአጠቃላይ በየአመቱ የገጠር መንገዶች ያሉበት ሁኔታ ተቋማዊ በሆነ መልኩ ጥናት በማድረግ ፍትሃዊ የበጀት ክፍፍል እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ተቋማትንማጠናከር፣የተቀናጀመረጃመሰብሰብ፣ለጥገናየሚውለውንየበጀትክፍፍልበተበላሸውመንገድልክፍትሃዊእንዲሆናሌሎችየመፍትሄሃሳቦችንአቅርበዋል። በደቡብ ክልልና በሃሳዋ ከተማ ስር የሚገኙ መንገዶች ሁኔታና ለመንገዶች የተበጀተው በጀት ተመጣጣኝነት ላይ የተደረገውን ጥናት ያቀረቡት በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ ሮቤል ደስታ ናቸው። በጥናቱ ግኝት መሰረት የመንገድ ርዝመትን ጨምሮ በሪፖርት የሚገለጸውና በተግባር የተገኘው ውጤት የተለያየ ነው። በክልሉ የሚገኙ አብዛኞቹ መንገዶች የተጎዱ መሆኑን በጥናቱ መለየቱን ገልጸው ይህ የሆነውም ትክክለኛ መረጃ ያለው የመንገድ አስተዳደር አለመኖሩን በምክንያትነት ያቀርባሉ። በመሆኑምበቀጣይየገጠርመንገድአስተዳደርየአየርካርታንመሰረትያደረገመረጃመኖርእንዳለበትሙያዊአስተያየታቸውንሰጥተዋል። በመንገዶች ላይ ያለው ወቅታዊ ሁኔታና ከመንገድ ፈንድ ለክልሉ የሚሰጠው በጀትም ተመጣጣኝ አለመሆን የሚፈለገውን ያህል ውጤት እንዳይመጣ አድርጎታል ይላሉ። የመንገዶች ርዝመት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ ድልድዮችና የተበላሹ መንገዶና እድሳት የሚያስፈልጋቸውን መረጃ በጥናት በመለየት በጀትን በአግባቡ መጠቀም ይቻላል ሲሉም ይመክራሉ። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ መምህር አቶ ህላዊ ምንዋጋው በበኩላቸው በክልሉ የሚገኙ የመንገድ ፈንድ ኤጀንሲዎች ለመንገድ ጥገና የሚጠይቁት በጀት ሳይንሳዊ በሆነና ችግሩን መሰረት ያደረገ አለመሆኑ በጥናቱ መለየቱን ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ኢሉአባቦራና ቡርኖ በደሌ ጥናቱን ያደረገው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለጥገና የሚጠየቀው ገንዘብ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል። የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ጽህፈት ዋና ዳሬክተር አቶ ረሽድ መሃመድ የክልል የገጠር መንገዶች ያሉበትን ሁኔታና ርዝመት በትክክል ካልታወቀ በጀት ለመያዝ እንደሚያስቸግር ያነሳሉ። በመሆኑም በጥናቱ የተገኘው ውጤት በቀጣይ ከመንገድ ፈንድ በጀት ሲመደብ ለእያንዳንዱ ክልል ፍትሃዊ የበጀት ክፍፍል ለማድረግ ይረዳል። እንደ ዋና ዳሬክተሩ ገለጻ በቀጣዩ ዓመት የመንገዶችን ደረጃ ለማሳደግና ጥገና ለማድረግ በሚያስችል መልኩ ለማቀድ ጥናቱ ያግዛል። በበአሰራርአደረጃጀትናበሰውሃይልበኩልየሚስተዋለውንየአቅምክፍተትበጥናቱመሰረትየሚስተካከልይሆናልብለዋል። በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ከችግሩ ስፋት አኳያ ቅደም ተከተል እየሰጠን እንሰራለን ሲሉም ጨምረዋል። በጥናቱ ያልተካተቱ ክልሎች በቀጣይ ከዚህ ተሞክሮ በመውሰድ የአገሪቱ አጠቃላይ መረጃ ይደራጃል ተብሏል። የኢትዮጵያ የመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት የመንገድ ጥገናና ደህነት ወጪን ለመሸፈን የተቋቋመ ነው። ከተሽከርካሪዎችናመንገድተጠቃሚዎችእንዲሁምበነዳጅላይከተጣለታሪፍበአመትከ2 ቢሊዮንብርበላይበመሰብሰብ 30 ሺህኪሎ ሜትርየፌዴራል፣ክልልናየከተማመንገዶችንጥገናናደህንነትተግባርእንደሚያከናውንምተገልጿል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም