የጣልያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አክሱም ገቡ

121
ሰኔ 14/2011 የጣልያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤላ ሲ ዴልሪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አክሱም ከተማ ገቡ ። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አክሱም ከተማ ሲደርሱ በከተማው ነዋሪዎችና በትግራይ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባባል ተደርጎላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት ሚኒስትሯ በአክሱም ኃውልት ተገኝተው ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ ። ከጉብኝቱ በኋላ ከፍተኛ ስጋት ለተደቀነበት አክሱም ኃውልት ጥገና ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ የጣልያን መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም