የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በ2012 ረቂቅ በጀት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

39
መቀሌ ሰኔ 13 / 2011 የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የበጀትና ኦዲት ቋሚ ኮሚቴ ለ2012 እንዲውል በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ተወያየ። ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የበጀትና ኦዲት ቋሚ ኮሚቴ ለ2012 እንዲውል በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ተወያየ። በውይይቱ ላይ ለበጀት ዓመቱ 16 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ማቅረቡን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሐጎስ ወልደ ኪዳን አስረድተዋል። ረቂቅ በጀቱ ካለፈው  በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ2ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል። የበጀት ጭማሪ ያሳየው በክልሉ የገቢ ግብር የመሰብሰብ አቅም በማደጉ ፣ወጪ ቆጣቢ አሰራር በመተግበሩና የሕዝብ ድጋፍ በማደጉ መሆኑን አስረድተዋል። ከቀረበው ረቂቅ በጀት 61 በመቶ የሚሆነው ለድህነት ተኮር ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ይውላል። በዋነኛነትም ወጣቶችና ሴቶች ማዕከል አድርጎ ለሚከናወኑ ሥራዎችማስፈጸሚያ ይሆናል ብለዋል። ክልሉ ግብር የመሰብሰብ አቅሙ ማሳደግ እንዳለበትና የኅብረተሰቡ የቁጠባ ባህል በማጎልበት የክልሉ በጀት በማሳደግ ሊረባረብ እንደሚገባ ባለድርሻ አካላቱ በውይይታቸው ትኩረት ሰጥተውበታል ። በረቂቅ በጀቱ ውይይት ከተሳተፉት መካከል ከሲቪል ማህበራት ጥምረት አቶ ዘሚካኤል ገብረመድህን ከግማሽ በላይ የሚሆን በጀት ለድህነት ተኮር መመደቡ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም