ኢትዮጵያ ለስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች - ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

60
አዲስ አበባ ሰኔ 12/2011 ኢትዮጵያ ለስደተኞች የምታደርገውን እንክብካቤና ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ። እንደአውሮፓውያንአቆጣጠርበ1969በቀድሞየአፍሪካኅብረትበመጠለያየሚገኙስደተኞችንለመንከባከብሥምምነት የተደረሰበት 50ኛዓመትዛሬተከብሯል። በዚሁ ወቅት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ28 አገራት የተውጣጡ ከ900 ሺ በላይ ስደተኞችን በተለያዩ የአገሪቷ ክልሎች አስጠልላለች። በርካታዎቹ ስደተኞች ኢትዮጵያን በድንበር ከሚዋሰኑት የጎሮቤት አገራት እንደሚመጡና መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገላቸው እነደሆነም ገልጸዋል። በተለይም ደግሞ ከመጠለያ ጣቢያ ተመዝግበው በመውጣት ከዜጎች እኩል የተለየዩ ማኅበራዊ አገልገሎቶችንእንዲያገኙ ለማድረግ እየሰራች መሆኑን ነው የገለጹት። ከአነዚህ አገልግሎቶች መካከልም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት የሥራ እድል እንዲያገኙ ማድረግ እንዲሁም የትምህርትና የመንጃ ፍቃድ ስልጠና ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሰራቱን ለአብነት አንስተዋል። መንግሥት በእነዚህ በተጠቀሱት ተግባራት ላይ አጠናክሮ እንደሚሰራበት ገልጸው አጠቃላይ የስደተኞችን ችግር ለመፍታት ግን በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ገልጸዋል። በተለይም ደግሞ ለስደት ምክንያት የሆኑትን ግጭት፣ ድህነት፣ የአየር ንብረት ለውጥን ወዘተ ለመከላከል የአፍሪካ አባል አገራት ተቀናጅተው መሥራት አለባቸው ብለዋል። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ ማሃማት በበኩላቸው" ስደትን ለመከላከል የአፍሪካ አባል አገራት በተናጠልና በጋራ የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከር አለባቸው።" ከዚህ ባለፈ የህግ የበላይነትን በማስከበር ግጭት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ሌሎች ስደትን የሚቀሰቅሱ ጉዳዮችን መግታት እንደሚገባም አሳስበዋል። በተለይም ደግሞ ግጭቶችና ሌሎች ማኅበራዊ ቀውስ የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞና በመረጃ ላይ ተመርኩዞ የቅድመ መከላከል ሥራ መሥራት ይገባል ብለዋል። የአፍሪካ ኅብረት በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚሰራቸውም ሥራዎችም እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ደጋፊ መሆናቸውን ነው ያስረዱት። በተለይም ደግሞ ሴቶችን ማዕከል አድርጎ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመው በሥራዎቻቸውም ዋነኛ ተዋናይ መሆን እንዳለባቸው ጠቁመዋል። በአሁኑወቅትበአፍሪካከ7 ሚሊዮንበላይስደተኞችበመጠለያጣቢያይገኛሉ። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1994 በአህጉሪተ ከተመዘገበው 11 ሚሊዮን ስደተኛ ቀጥሎ ከፍተኛው ቁጥር ነው ተብሏል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም