እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተጠርተው እንዲቀርቡ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ደብዳቤ እንዲጻፍ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተጠርተው እንዲቀርቡ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ደብዳቤ እንዲጻፍ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ
74
ሰኔ 12/2011 እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተጠርተው እንዲቀርቡ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ደብዳቤ እንዲጻፍ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ በእነ ጌታቸው አሰፋ ላይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው የምስክሮች ጥበቃ አቤቱታ ተሻሽሎእንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ። ተከሳሾች በምርመራ ጊዜም ሆነ አሁን ቋሚ አድራሻ የሌላቸው በመሆኑ ክሱ ከ12 ዓመታት በላይ የሚያስቀጣ በመሆኑ በወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 161 እና 162 አማካኝነት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጥሪያው እንዲወጣ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተከሳሾች በእነ አቶ ጌታቸው መዝገብ 1ኛ፣ 9ኛ፣ 11ኛ እና 12ኛ በጋዜጣ የሚወጣላቸው ጥሪ እንዲደርሳቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲጠሩ ለማድረግ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ደብዳቤ እንዲደርሰው ፍርድ ቤቱ አዟል። የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ቃል ለመስማት ለሐምሌ 18፣ 23፣ 24፣ 25 እና 30 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በጋዜጣ ጥሪ መጠባበቅና ዐቃቤ ህግ አሻሽሎ ያቀረበውን የምስክሮች ጥበቃ አቤቱታ ለመስማት ለሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷል።