ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢኳሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንትን ተቀብለው አነጋገሩ

278

አዲስ አበባ ሰኔ 12/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኙትን የኢኳሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ኦቢያንግን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ፕሬዝዳንቱ  ለይፋዊ ጉብኝት ያሳለፍነው ሰኞ  አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ኦቢያንግ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታም  በሁለትዮሽ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ  መክረዋል።

ፕሬዝዳንት ቴዎዶር አቢያንግ ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋርም ተገናኝተው በሁለትዮኝ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያና ኢኳቶሪያል ጊኒ ግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል ዕድሜ ያለውና ዘርፈ ብዙ የጋራ ስምምነቶች የተፈረሙበት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው።