በምዕራብ ሸዋ በፈተና ማጭበርበር 16 ሰዎች በእስራት ተቀጡ

66
ሰኔ 11/2011  በምዕራቅ ሸዋ ዞን የአቡና ግንደበረት ወረዳ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት በተካሔደው የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የማጭበርበር ድርጊት ፈፅመዋል ያላቸው 16 ሰዎች በእስራት እንዲቀጡ መወሰኑን አስታወቀ ። የወረዳው ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ መንግስቱ ጫላ እንዳሰታወቁት ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የእስር ቅጣቱን ያስተላለፈው ሌሎች እንዲፈተኑላቸው ባደረጉ 4 የፖሊስ አባላትና ለሌሎች ሲፈተኑ በተገኙ 12 ሰዎች ላይ ነው ። በዛሬው ችሎት ጉዳዩን የተመለከተው የወረዳው ፍርድ ቤት አራቱ የፖሊስ አባላት እያንዳንዳቸው በስድስት ወር እስራት ሌሎቹ 12 ሰዎች ደግሞ በአራት ወር እስራት አንዲቀጡ ወስኗል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም