በመላው አገሪቱ ሲሰጥ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተጠናቀቀ

75
ሰኔ 11/2011 በመላው አገሪቱ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ከሰኔ 6 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ፈተናው ሲሰጥ የቆየው። ሚኒስቴሩ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉ መምህራን፤ ተማሪዎች፣ የትምህርት አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ ወላጆች፣ የፀጥታ አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቅርቧል። ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች መልካም ውጤት እንዲገጥማቸው በመመኘትም በእረፍት ጊዜያቸው ታናናሾቻቸውን በማስጠናት፣ ወላጆቻቸውን በመርዳትና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በመሰማራት አርዓያ እንዲሆኑም ጥሪ አስተላልፏል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም