በትግራይ 255 ማህበራት ወደ መካከለኛ ባሃለሀብትነት ሊሸጋገሩ ነው

66
ሰኔ 10/2011 በትግራይ ክልል 255 ማህበራት ወደ መካከለኛ ባለሃብትነት የሚሸጋገሩበት መድረክ መዘጋጀቱን የክልሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተቋማትና የከተማ ምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ኤጀንሲ አስታወቀ ። የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር አቶ ገብረመድህን ሐጎስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት በሚከበረው የክልሉ የሰማእታት ቀን ምክንያት በማድረግ 255 አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት ወደ መካከለኛ ባለሃብትነት እንዲሸጋገሩ ይደረጋል ። "በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ሥራ የተሰማሩ 30 ሞዴል ማህበራትም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እውቅና ይሰጣቸዋል" ብለዋል። በተጫማሪም ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላትና  ተቋማት ምስጋና የሚሰጣቸው መሆኑን አቶ ገብረመድህን የገለጹት። በበዓሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ያዘጋጁት ኤግዚቢሽንና ባዛርን ጨምሮ የክልል ከፍተኛ አመራሮች የሚሳተፉበት ኮንፈረንስ መዘጋጀቱ ታውቋል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም