የሃኪሞች ቡድን በአዲስ አበባ ነጻ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው

67
ሰኔ 10 / 2011 መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የሃኪሞች ቡድን በአዲስ አበባ ነጻ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። የጁዊስ ቮይስ ሚኒስትሪ ኢንተርናሽናል ግብረ ሰናይ የሃኪሞች ቡድን ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ታካሚዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ሰሞኑን አዲስ አበባ ገብተዋል ከ100 በላይ የህክምና አባላትን ይዞ ወደ አዲስ አበባ የገባው የሃኪሞች ቡድን በህዳሴ ጤና ጣቢያ ከትናንት ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የጁዊስ ቮይስ ሚኒስትሪ ኢንተርናሽናል ተወካይና ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ በራሳ ተናግረዋል። የጥርስ፣ የዐይንና የቆዳ መለስተኛ ቀዶ ህክምናና የጽንስ የውስጥ ደዌና የቪዚዮቴራፒ እንዲሁም ሌሎች የስኳርና የደም ግፊት ህክምናዎች እንደሚሰጡም ተናግረዋል። ህክምናው በዋናነት የሚሰጠው ከፍሎ መታከም ለማይችልና አገልግሎቱን ፈልጎ ለመጡ ታካሚ መሆኑን ተናግረዋል ዳይረክተሩ። እንደ ዳይረክተሩ ገለጻ የህክምና ቡድኑ በየዓመቱ እየመጡ ግልጋሎቱን እንደሚሰጡ ተናግረው ይህንን ህክምናም በአካባቢው ሲሰጥ ለአስራ አምስተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል። ተከታታይ የህክምና አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ከሌሎች የግል ህክምና ተቋማት ህክምናቸውን  እስኪጨርሱ የሀክምና ወጪያቸው ይሸፈናል። የጤና ጣቢያው ኃላፊ ደሳለኝ ታደሰ  በበኩላቸው በተቋሙ የታካሚዎች ፍሰት ከፍተኛና ከፍለው መታከም የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በብዛት ያሉበት ነው። አሁን እየተደረገ ያለው ህክምና ከፍለው መታከም ለማይችሉ ሆነው መድሃኒትና ሌሎች የተለያያ የህክምና አገልግልቶችንም በቅርበት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተናግረዋል። የጤና ጣቢያው ሰራተኞችም ከሚመጣው የሃኪም ቡድን ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ ለመቅሰም እንደረዳቸውም ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም