በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ችግኝ ተተከለ

110

ሰኔ 10 / 2011 ሠራተኞቹ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አነሳሽነት በመካሄድ ላይ ያለውን አገራዊ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በመደገፍ የዛሬውን ጨምሮ በተለያዩ ፕሮግራሞች 450 አገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል።

የብሔራዊ ቤተ መንግስት ቅጥር ግቢ ከንጉሣዊው ሥርዓት ጀምሮ የተተከሉ ዕድሜ ጠገብ ዛፎች የሚገኙበት ሲሆን ዛሬ የተተከሉትም የቆዩትንና በተለያየ ምክንያት የሚጠፉትን መተካት የሚችሉ ናቸው።

የቤተ መንግሥቱ ሠራተኞች ከተከሏቸው የችግኝ አይነቶች መካከል ዝግባ፣ ዋርካ፣ ግራር፣ ፅድና ሌሎችም አገር በቀል እፅዋት ይገኙበታል።

ሠራተኞቹ ችግኞቹን በቋሚነት የሚንከባከብ አካል ቢኖርም በእኔነትት ስሜ ትእንደሚንከባከቧቸው ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞች ከሚኒስትሩ ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በመሆን በመስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።