ወጣቱ አክራሪ ብሔርተኝነትን እንዲዋጋ ተጠየቀ

84
ባህር ዳር ሰኔ 10/2011 ወጣቱ ትውልድ አክራሪ ብሔርተኝነትን በመዋጋት ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት እንዲለመልም ትኩረት ሊያደርግ ይገባል ተባለ። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ  ቢሮ ከአፋርና ከኦሮሚያ አጎራባች ተመሳሳይ ቢሮዎች ጋር በመተባበር ”አንድነታችን ለዘላቂ ልማታችን ” በሚል መሪ ሃሳብ በባህ ዳር ከተማ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ዛሬ ተካሂዷል። የአማራ ክልል ሴቶች፣ህጻናትናወጣቶችጉዳይቢሮኃላፊወይዘሮአስናቁድረስበምክክርመድረኩላይእንደገለጹት ኢትዮጵያውያንበደምናበአጥንትየተሳሰሩናከግልመገለጫቸውይልቅየጋራየሆነመለያቸውይበዛሉ። በኢትዮጵያ በየጊዜው በተከሰቱት የለውጥ ሂደቶች ላይ የወጣቶችና የሴቶች ድርሻ የጎላ መሆኑን አስታውሰዋል ። "አሁን እንደአገር ለመጣው ለውጥ በርካታ ሴቶችና ወጣቶች እስከ ህይወት መስዋዕትነት ዋጋ ከፍለውበታል" ያሉት ኃላፊዋ ለውጡን የማይፈልጉ አካላት ሒደቱን ለመቀልበስ ወጣቱን መጠቀሚያ እያደረጉት መሆኑን ገልጸዋል ። አክራሪ ብሔርተኝነት በሃገሪቱ በሰፊው እየተሰበከ መሆኑን የተናገሩት ወይዘሮ አስናቁ ወጣቱን ትውልድ መጠቀሚያ ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ሩጫ በጋራ መከላከል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ። ወጣቱ መስዋዕትነት ከፍሎ ያመጣው ለውጥ ለዴሞክሪሲያዊ ብሔርተኝነት እንጂ ለአክራሪ ብሔርተኝነት አለመሆኑንም አስገንዝበዋል። የምክክር መድረኩ ዓላማ ወጣቱ አክራሪ ብሔርተኝነት ለኢትዮጵያ እንደማይጠቅም አውቆ በጋራ ለአገር ደህንነት እንዲሰራ የሚያስችል እድል ለማመቻቸት መሆኑም ተመልክቷል። "ሴቶች በተፈጥሮ የታደልነውን ርህራሔና የማስተዳደር ጥበብ ለሃገር ግንባታ ልናውለው ይገባል" ያሉት ደግሞ የሴቶች ፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ ናቸው ። "ኢትዮጵያዊያን በደም የተሳሰሩ በመሆኑ በጥቃቅን ጉዳዮች ለመለያየት የሚፈልጉ አካላት መቼም ቢሆን አይሳካላቸውም" ብለዋል  ። ወጣቱ ትውልድ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ የሚነገረውን ብቻ በመቀበል ለሀገራዊ አንድነት ፀር የሆኑ አስተሳሰቦች ሰለባ ከመሆን ራሱን እንዲከላከልም ምክረ ሃሳብ ተለግሷል በመድረኩ ። ሴቶችና ወጣቶች በአገራዊ ግንባታ ላይ በጋራ እንዲመክሩና እንዲሰሩ እንደሃገር ውስንነት መኖሩን የገለፀችው ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል የመጣችው ወጣት አይዛ አብዱልቃድር ናት። ወጣቱ በምክንያታዊነት ላይ ተመስርቶ  ሃሳቡን እንዲያራምድ የክልሎች የእርስ በእርስ የምክክር መድረክ መስፋት እንዳለበት ጠቁማለች ። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ተሞክሮን ሁሉም ክልሎች ሊጋሩት እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ የአፋር ክልል ሴቶች ፣ ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ የሴቶች አደረጃጀት ዳይሬክተር ወይዘሮ ፋጡማ አፈረ ናቸው ። ወጣቱ በአንድነትና በዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ላይ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖረው ከተፈለገ ሁሉም ወገኖች በግንዛቤ ማጠናከሪያ ትምህርት ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባ ተመልክቷል ። በምክክር መድረኩ ላይ የክልልና የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች ጨምሮ የአፋር ፣ የኦሮሚያና የአማራ ክልል ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አመራሮች ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም