የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አባት አረፉ

72
ሰኔ 8/2011 የዶክተር አብይ አህመድ አባት አቶ አህመድ አሊ ባደረባቸው ህመም በጅማ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ አረፉ ። የአጋሮ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ ጌታቸው ጎዳና እንደገለጹት አቶ አህመድ አሊ ወይም አባፊጣ አባናሳ ባደረባቸው ህመም በጅማ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ አርፈዋል።
አስከሬናቸውም ዛሬ ወደ አጋሮ-በሻሻ የተወሰደ ሲሆን በነገው እለትም የቀብር ስነ-ስርዓቱ ይፈጸማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም