ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሰአት በኋላም በሲኤምሲ አደባባይ ችግኝ ተክለዋል

130
ሰኔ 9/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲኤምሲ /CMC/ አደባባይ ችግኝ ተክለዋል። በችግኝ ተከላው ከጠቅላይ ሚስትር አብይ እና ቀዳማዊ እመቤ ዝናሽ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን በአገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ የደን ልማት ንቅናቄና የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደሚከናወን ከዚህ ቀደም መግለጹ የሚታወስ ነው። ይህም በችግኞች ፅድቀት ተግዳሮቶች ምክንያት የከሰሙና የቀጨጩ ችግኞችን በተሻሻለ ሁኔታ ለመተካት ያለመ መሆኑም ተገልጾ ነበር። በዚህ መርሃ ግብር ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎት እየተሳተፉ ይገኛሉ። በዛሬው እለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማለዳ 1 30 ላይ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጽዳትና ችግኝ ተከላ ያደረጉ ሲሆን ከሰዓት በኋላም በCMC አደባባይ ችግኝ ተክለዋል። ኢንጅነር ታከለ ኡማም ማለዳ በልደታ ክፍለ ከተማ የፅዳት መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ የችግኝ ተከላም አከናውነው ነበር። በብሔራዊ የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም መርሃ ግብር በዘንድሮው ክረምት በመላ አገሪቷ 4 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ተመድቧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም