ባንኩ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቃዮች ከ3ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

46
ሰኔ 8/2011የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቤልኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቃዮች ከ3ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ። የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና ዛሬ ገንዘቡን በአሶሳ ከተማ ለክልሉ መንግስት ባስረከበቡበት ወቅት እንዳሉት የገንዘብ ድጋፉ ባንኩ ከተፈናቃዮቹ ጎን መቆሙን ለማሳየት ነው። “ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ቤኒሻንጉል ጉሙዝን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በ70 ሚሊዮን ብር እያስገነባቸው የሚገኙትን የጤና ተቋማት ለአብነት ጠቅሰዋል። በቀጣይም ባንኩ ለህብረተሰቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ በበኩላቸው ባንኩ ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ባንኩ ተደራሽነቱን በማስፋት ለክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መጠናከር የሚያደርገውን ተሳትም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ አመት በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም