የአዲስ አበባ የ6ኛ ኮርስ አባላት 20ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ ደም ለገሱ

79
ሰኔ 8/2011   የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 6ኛ ኮርስ አባላት 20ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ አደረጉ። የኮሚሽኑ 6ኛ ኮርስ ምሩቅ የነበሩት አሁን በኮሚሽኑ አባል የሆኑትና በሌሎች የስራ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ዛሬ በብሔራዊ ደም ባንክ በመገኘት ደም ለግሰዋል። በደም ልገሳ ላይ የተገኙት የኮርሱ አባላት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኮርሳቸውን ካጠናቀቁ ከ20 ዓመት በኋላ ተገናኝተው የደም ልገሳ ለማድረግ በቅተዋል። በቀጣይም በየሶሰት ወሩ በመገኘት ደም በመደበኛነት እንደሚለግሱ ጠቁመው በቀጣይ በሌሎች በጎ አድሯጎት ስራዎች ላይ እንደሚሳተፉም ገልጸዋል። የደም ልገሳ ተግባራቸው ወደፊት እንደሚቀጥል ገልጸው እንደነሱ ሁሉ ሌሎች ምሩቃን ሆኑ ህብረተሰቡ የደምልገሳ ላይ በስፋት እንዲሳተፍ ለማበረታታት ያግዛል ብለዋል። ሌላው ደም ለጋሽ አቶ ደሳለኝ ስዩም እንደሚሉት፤ በአሁኑ ወቅት ከፖሊስነት ሙያቸው ቢወጡም ከኮርስ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ማህበራዊ አገልግሎት የመወጣት ግዴታቸውን አልዘነጉም። በቀጣይም ሌሎች ጓደኞቻቸውንና ህብረተሰቡን ለማገልገል እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል። በብሔራዊ ደም ባንክ ደም ባለሙያ የሆኑት አቶ አሳየ ጥላሁን በበኩላቸው የ6ኛ ኮስርስ ምሩቃን በቡድን ያደረጉት የደም ልገሳ የሚበረታታና ለሌሎችአረዓያ መሆኑን ገልጸው የደም ለጋሽ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም ከፍላጎቱ አንጻር ብዙ እንደሚቀር ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስድስተኛ ኮርስ አባላት የነበሩት 630 ሲሆኑ በ1991 ዓ.ም ተመርቀው ወደስራ የተሰማሩ ናቸው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም