የፌዴራል ተቋማት ድረ-ገጾች ወቅታዊ መረጃ የማሰራጨት ክፍተት አለባቸው - ኢዜአ

114
አዲስ አበባ ሰኔ /2011  የፌዴራል ተቋማት ድረ-ገጾች ወቅታዊ መረጃ በማሰራጨትና የተጠቃሚውን እርካታ ማሟላት የማይችሉ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ። የችግሩ መንስኤ ብቃት ያለው የዘርፉ ባለሙያ እጥረት፣ የአሰራርና የአደረጃጀት ውስንነት፣ የመሰረተ -ልማት አለመሟላት መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ግልጸዋል። ኢዜአ የፌዴራል መሥሪያ ቤት ተቋማት የድህረ-ገጽ አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ የሰራውን ጥናት ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች አቅርቧል። ውይይቱ ''በለውጥ ውስጥ ባለ ማኅበረሰሕብ ዘንድ የመረጃ ተደራሽነት ለማረጋገጥ የኮሙኒኬሽንና የመገናኛ ብዙኃን ሚና'' በሚል ርዕስ ትናንት በአዳማ የተጀመረው ሥልጠና አካል ነው። በውይይቱ ላይ እንደተገለጸው፤ የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት ድረ-ገፆች በይዘት ያልበለጸጉ፣ ወቅታዊ መረጃ የሌላቸው፣ ገጸ-ውበቱ ተመልካችን የማይስብና የተቋማቱንም ተልዕኮ የማያሳዩ ናቸው። ጥናቱ የተካሄደው በድረ-ገፆችወቅታዊመረጃለማስተላለፍናለኅብረተሰቡመረጃ በሃላፊነትለማድረስ የድኅረ-ገጽመሰረተ-ልማት የገነቡሃ ያሚኒስትቴርመሥሪያቤቶች ናቸው። የኢዜአ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ ፈለቀ ሽኩር እንደገለጹት፤ ለኅብረተሰቡ መረጃ ከሚለቁት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መካከል ከአንዱ በስተቀር ተጠቃሚዎችን ስለማርካት የሚያውቀው ነገር የለም። አብዛኞቹ መሥሪያ ቤቶች ጥናት እንደማያካሂዱና ደካማ የአስተያየት ወይም የግብረ መልስ ሥርዓት እንዳላቸው ነው የተናገሩት። ብቁ ባለሙያ አለመኖር፣ መረጃን ለድረ-ገጽ የመጫንና የማውረድ ተግባር በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ክፍል መካሄድ፣ የኢንተርኔት መቆራረጥ፣ ይህንንም ተከትሎ የድረ -ገጾች አገልገሎት መስጠት ማቆም እንደ ችግር በጥናቱ ተጠቁሟል። በጥናቱ ከድረ -ገጾች የሚፈለገውን መረጃ በቀላሉ ለማውረድ፣ አስተያየቶችን ለመጫንና ተግባራቱን በቅልጥፍና ለማከናወን የሚችሉ አራት የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ድረ-ገጾች ብቻ መሆናቸውን ጥናቱ አመላክቷል። አቶ ፈለቀ እንደገለጹት፤ የሌሎች መሥሪያ ቤቶች ድረ-ገጾች ለመክፈት የሚዘገዩ፣ የጽሁፍና የምስል መረጃዎችን በፍጥነት ለመክፈትና ለማውረድ የሚያስቸግሩ የመረጃ ቋታቸው ባዶ የሆነ ወይም ወቅታዊ መረጃ የሌላቸው ናቸው። የአብዛኞቹ ተቋማት ድረ ገጾች በሕዝብ ግንኙነት ሳይሆን በኢንፎርሜሽን ኮኒኬሽን ባለሙያዎች እንዲያዙ መደረጉ ለችግሮቹ መንስኤ መሆኑን አመላክተዋል። በውይይቱ ኃሳባቸውን የሰጡ የህዝበ ግንኙነት ባለሙያዎች ለድረ-ገጾች አዳዲስ መረጃዎችን ከማቅረብ አኳያ ችግር አንዳለ አምነው፤የአደረጃጀት፣ የአሰራር፣ የዘርፉ ባለሙያ በቦታው ያለመመደብና ብቃት ያለው ባለሙያ አለመኖር ዋነኛው ተግዳሮት መሆናቸውን ተናግረዋል። ድረ-ገጹን የይዘት ማበልጸጊያ፣ መረጃ ማቅረቢያ አድርጎ ከማየት ይልቅ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ተግባር አድርጎ የመውሰድ አዝማሚያ ሥራውን በተገቢው መልኩ ለማከናወን እንቅፋት እንደሆነም ተጠቁሟል። መረጃዎችን ለመጫንና ለማውረድ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በየጊዜው መጠየቅና የሚያስፈልግ መሆኑን ከአሰራሩ አስቸጋሪነት አንጻር ስራውን ፈታኝ አድርጎታል። እነዚህ እንዳሉ ሆኖ መሰረታዊ ችግሮች ሆኖ የሚታየው የፖርታል ምቹ አለመሆን፣ የመረጃ ቋቱና ሌሎች መሰረተ ልማት አለመሟላት ችግሩን ይበልጥ ማባባሱን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት አገር ውስጥ ያለውን ፖርታል ተገቢውን እውቅና (አይ ፒ) ለማግኘት ከሚወስደው ይልቅ የፌስ ቡክና የትዊተር ተቋማትን እውቅና እንዲሰጡ ለማድረገ ቀላል ሆኖ መገኘቱን ጠቁመዋል። ጥናቱ ባመላከተው ምክረ ሃሳብ መሰረት ችግሩን ለመፍታት ባለሙያዎችን በብቃት ማሰልጠን፣ የውጭ አቅምን መጠቀምና የድረ-ገጹን አስተዳደር ለህዝብ ግንኙነት መልቀቅ እንዲሁም ድረ-ገጹን እንደ ፌስቡክ ካሉ ገጾች ጋር ማስተሳሰር ያስፈልጋል። የኢዜአ ዋና ዳይሬክተር አቶ በቀለ ሙለታ በበኩላቸው ጥናቱ ትኩረት ያደረገው በመሰረተ ልማት ጉዳዮች ላይ ሳይሆን በይዘትና በገጸ-ውበት (በዲዛይን) ላይ ነው። በአሁኑወቅትወደዲጂታልኮሙኒኬሽንሽግግርእየተደረገበመሆኑአሁንላይያለውየኮሙኒኬሽንባለሙያየዲጂታልኮሙኒኬሽንኃይልሆኖመምጣትእንዳለበትአስገንዝበዋል። በዚህ ረገድ ኢዜአ በይዘትና በገጸ-ውበት (ዲዛይን) ለማማከርና ለማገዝ የሚያስችል አቅም እንደፈጠረና አብሮ ለመስራትም ፍላጎት እንዳለው አስረድተዋል። ኢዜአየድረገጽይዘትእንዲበለጽጉ፣መረጃዎችበፍጥነትእንዲደርሱተቋሙበህግየተሰጠውተልዕኮመሆኑንአመላክተዋል።                
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም