የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት በባሌ ዞን መደወላቡና ደሎመና ወረዳዎች የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

118
ሰኔ 8/2011 የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መደወላቡና ደሎመና ወረዳዎች ተገኝተው የመሰረተ ልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው። ምክትል ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው በመደወላቡ ወረዳ የተገነባውን የመደወላቡ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን መርቀው ሥራ ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም በደሎመና ለሚገነባው የመስኖ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ታውቋል። በምክትል ፕሬዚዳንቱ የመሰረተ ልማት ጉብኝት ላይ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (. የኦዲፒ) ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸው ተመልክቷል። አቶ ሽመልስ በትናንትናው ዕለት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ በባሌ ሮቤ ከተማ ከሕብረተሰቡ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል። በተጨማሪም የኦሮሚያ ብሮድካስቲግ ኔትወርክ (ኦ.ቢ.ኤን )የባሌኤፍ.ኤምሬድዮናቴሌቪዥን ስርጭት የሚሆን ስቱዲዮ ለመገንባት  በባሌ ሮቤ ከተማ የመሰረት ድንጋይ እንዳስቀመጡ  መዘገቡ  ይተወሳል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም