የትግራይ ክልል ፖሊስ የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ሀላፊ አቶ ጌታቸው አስፋን አድራሻ እንደማያውቅ ገለጸ

62
ሰኔ 3/2011 የትግራይ ክልል ፖሊስ የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አስፋን አድራሻ እንደማያውቅ ገለጸ። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፖሊስ አቶ ጌታቸው አስፋን ጨምሮ ለ3 ሰዎች መጥሪያ እንዲያደርስ ለ 2 ጊዜ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። በዚህ መሰረት  የፌደራል ፖሊስ ለትግራይ ክልል ፖሊስ ለተከሳሾቹ የፍርድ ቤቱን መጥሪያ እንዲያደርስ በፋክስ የላከለት ደብዳቤ 'ትግራይ ክልል' ከማለት ዉጭ እርግጠኛ አድራሻቸውን የማይገልፅ በመሆኑ የተከሳሾቹን አድራሻ ለማወቅ እንደማይችል ነው የገለጸው። አቃቢ ህግም ተከሳሾቹ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ 12 ዓመት የሚያስቀጣቸው ወንጀል በመፈጸማቸው ለተከሳሾቹ በየጋዜጣው ጥሪ እንዲደረግና ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም ተከሳሾቹ በጋዜጣ ጥሪ' ይደረግላቸው፣አይደረግላቸው ወይም ድጋሚ መጥሪያ ይላክላቸው፤ አይላክላቸው' በሚለው ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሰኔ 12 ቀን 2011 ቀጠሮ ሰጥቷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም