ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በ2019/20 ሁለት ነጥብ ዘጠኝ በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘግባሉ - ዓለም ባንክ

64
ግንቦት 3/2011 ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት እአአ በ2019/20 ሁለት ነጥብ ዘጠኝ በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያስመዘግቡ የዓለም ባንክ ተነበየ። ለኢኮኖሚው እድገት የግብርና ምርትና ምርታማነት መነቃቃት መፈጠሩ፣ የነዳጅ ምርትና ኤክስፖርት ላይ መሻሻሎች መታየታቸውን እና ቀጣይነት ያለው የህዝብ ኢንቨስትመንት መነሻ እንደ ሆነ  መጠቀሱን ሲ ጂ ቲ ኤን በድረ ገጹ አስነብቧል። እንደ ድረገጹ ዘገባ ሀገራቱ በአውሮፓዊያኑ በ2020 ኢኮኖሚውን በማሻሻልና በማበልጸግ እድገቱ 3ነጥብ 3 በመቶ ከፍ እንደሚልም ተገልጿል፡፡ ከአገራቱ ዕድገት መካከል አንጎላ 2 ነጥብ 9 በመቶ፣ ደቡብ አፍሪካ በ1 ነጥብ 5 በመቶ እና ናይጀሪያ የ2ነጥብ 2 በመቶ ድርሻ እንደሚኖራቸውም ባንኩን ዋቢ በማድረግ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል። የየሀገራቱ ሀገራዊ የምርት ገቢ ላይ እድገት እንደሚመዘገብ የተገለጸ ቢሆንም፤ እድገቱ የቀጠናውን ድህነት ለመቀነስ በቂ እንዳልሆነ በዘገባው ተጠቅሷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም