'ምስጋና የተቸሩ ሃኪም'- ዶክተር ዘላለም ጭምዴሳ

142
በይሁኔ ይስማው /ኢዜአ/ ‘ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው’ እንዲል በጎ አድራጊው ቢኒያም በለጠ በየሙያ ዘርፉ ሰዎችን ለመርዳት፣ ማህበረሰባዊ ማነቆዎችን ለመቅረፍ የሚታትሩ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አብነት በሚባለስ ሰፈር ተወልደው ያደጉት በመጀመሪያ በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በአሁኑ ወቅት ደግሞ የዘውዲቱ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ዶክተር ዘላለምጭምዴሳ ‘በጉንችሬ ሆስፒታል’ ያደረጉት ተግባርም ሰዎችን ለመርዳት ሰው መሆን እንጂ ሌላ የተድላ ህይወት መኖርን የማይጠይቅ መሆኑን ያሳያል። የዶክተር ዘላለም መልካም ስራቸውን እነሆ ብለናል… የጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በጉራጌ ዞን እነሞርና ኤነር ወረዳ ውስጥ ይገኛል። በ2007 ዓ.ም የተመሰረተው ሆስፒታሉ በዙሪያው 72 ቀበሌዎችና አጎራባች ስፍራዎች ለሚገኙ ከ240 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አገልግሎት የመስጠት ተደራሽ ነው። የሆስፒታሉ ዋና ዳይሬከተር ዶክተር አማረ ግርማ ጉንችሬ የታካሚዎች ቁጥር ይብዛ እንጂ አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችሉ እንደ ኤክስሬይ ማሽን፣ አልጋ፣ ዊልቸር፣ የላቦራቶሪና ሌሎች የህክምና መስጫ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ እንደሌለው ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም የተሟላ የሰው ሃይልም ሆስፒታሉ እንደሌለው ይገልጻሉ። በዚህም በህክምና ቁሳቁሶችና በሰው ሃይል እጥረት የቀላል ህክምና ተጠቃሚዎች ሳይቀር በሆስፒታሉ አገልግሎት እርካታ እንደሌላቸው ያመለክታሉ። በጉንችሬ ሆስፒታል የደም ዩኒት የሚቀመጥበት ፍሪጅ የሌለው ሆስፒታሉ ደም ለሚያስፈልጋቸው ወላዶች አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ኪሎ ሜትር አቋርጦ ሆሳዕና ከተማ ድረስ ለመጓዝ ይገደድ ነበር። ይህንን ፋታ የማይሰጥ ችግር የተጋፈጠው የጉንችሬ ሆስፒታል ችግር ውስጥ መሆኑን የሰሙት ማስቀመጫ ባለመኖሩ ደም የሚፈሳት እናት ወደ ሆስፒታሉ የመጣች እናት ደም ለማገኘት በርካታ ኪሎሜትር በማቋረጥ ከሆሳዕና ከተማ በጊዜዊ ደም ማስቀመጫ ቦክስ ደም በማምጣት ነበር ህክምናው የሚሰጠው። ይህንን ፋታ የማይሰጥ የሆስፒታሉን ችግር የሰሙት ዶክተር ዘላለምዓቅማቸው የቻለውን ለማድረግ ለራሳቸው ቃል በመግባት የሆስፒታሉን የቁሳቁስ ችግር ሊፈታ የሚችል ተግባር አከናውነዋል። ዶክተር ዘላለም ከንፈር ከመምጠጥ ይልቅ በሰላ አእምሮቸው የችግሩን መፍትሄ አሰላሰሉ። በአይነ ህሊናቸው ወደ ውጭ በጎ አድራጊዎች ተመለከቱና በበይነ መርብ የመልክት ልውውጡን አጧጧፉት-የህክምና ቁሳቁስ ድጋፋ ለማገኘት። በእነሞርና ኤነር ወረዳ ከሚንቀሳቀስ 'ቅድሚያ' በሚል ስያሜ ከሚታወቅ መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎትማህበርና ከወረዳው የስራ ሃላፊዎች ጋር መከሩ። መክረውም ‘ኪዩር ፕሮጀክት’ ለተሰኘ የአሜሪካ ድርጅት በጻፉት ፕሮፖዛልም ይሁንታ አገኙ። የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፉም ተገኘ። ሆስፒታሉ ሲናፍቃቸው የነበሩ የደም ማስቀመጫ ፍሪጅ፣ የታካሚዎች አልጋ፣ ዊልቸር፣ የላብራቶሪ እቃዎችን ጨምሮ ግምቱ 13 ሚሊዮን ብር የሆነ ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ በጥረታቸው ተገኝቷል። ድጋፉ እንዲገኝ ላስተባበሩት ዶክተር ዘላለም ጭምዴሳም፣ የ'ቅድሚያ' በጎ አድራጎት ማህበር አስተባባሪ አቶ አስቻለው አበበ፣ የእነሞርና ኤነር ወረዳ ጤና ጽህፈትቤት ሀላፊ አቶ ሚፍታ በሀይሉም አሻራቸውን አስቀመጡ። ‘በጎ የሰራ የእጁን ያገኛልና’ ትናንት እነዚህ ግለሰቦች የምስጋናና እውቅና ተችሯቸዋል። ግለሰቦቹ በአካባቢዊነት ስሜት ሳይታጠሩ በኢትዮጵያዊነታቸው ኢትዮጵያዊ የሆነ መልካም ስራ በማከናወናቸው እጅ ተነስተዋል። ከተመስጋኞቹ መካከል የዘውዲቱ ሆስፒታል ዳይሬክተሩ ዶክተር ዘላለም ጭምዴሳ ’’ማንም ሰው ለአገሩ የሆነነገር ማበርከት ተብሎ ከታሰበ ሁሉም ነገር ይቻላል፤ ዋናው ነገር በጎ አሳቢ መሆን እንጂ ሌላው ብዙም አይከብድም” ነው ያሉት። በቀጣይም ሆስፒታሉን እንደሚያግዙ አረጋግጠዋል። በቀጣይም እንደ አገር መሰል የህክምና ቁሳቁስ በዓመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በጉንችሬ ሆስፒታልም የማህጸን ታካሚዎችና ሽንት መያዝ ለሚቸገሩ አረጋዊያንን በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር ከትቂት ቀናት በኋላ በነጻ ህክምና ለመሰጠት እንደሚሄዱም ነው ቃል ገብተዋል። የጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አማረ የተበረከቱ ቁሳቁሶች ከሆስፒታሉ ዘርፈ ብዙ ችግር አኳያ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳ ብዙ ችግሮችን እንደሚያቃልል ነው የገለጹት። በተለይም ተኝተውለሚታከሙ፣ ደም ለሚፈለጉ እናቶች እፎይታን ይፈጥራል ነው ያሉት። የኤክስሬይ ማሽን አለመኖርና በሰው ሃይል በኩልም የቤተ ሙከራ ሙያተኞች እጥረት የጉንችሬ ሆስፒታል ዛሬም ያልተፈቱ ችግሮች ናቸው። በሌሎች ታዳጊ አገሮች በጎ አድራጊ ድርጅቶች በማፈላለግ ይህን መሰል ደጋፍ የሚያገኙበትን እድል በአግባቡ ይጠቀማሉ። በጎረቤት ኬኒያም ይህን መሰል ስራ ያለ ሲሆን ከበጎ አድርጊ ድርጅቶች ይህን መሰል ድጋፍ ለማግኘት በኡሁሩ ኬኒያታ ባለቤት ማርጋሬት ዋንጅሩ ኬኒያታ ዋና አስተባባሪነት የሚከናወን ነው። ዶክተር ዘላለም ከዚህ በፊት ስራ በጀመሩበት ቦና ወረዳ የመጀመሪያ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ እንዲያገኝ የሚያስችል ተግባር አከናውነዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም