የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ባለፉት 50 ዓመታት በዘርፉ ልማት ጉልህ አስተዋፆ አበርክቷል

64
ሰኔ 30/2011  የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ባለፉት 50 ዓመታት በዘርፉ ጉልህ ሚና እንደነበረው ተገለጸ። የሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ማዕከል በ1961 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንግስት ከእስራኤል መንግስት ባገኘው ድጋፍ ተቋቋመ፡፡ በወቅቱ በሆቴልና ቱሪዝም መስክ የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ለማሟላት በሚል ተቋቁሞ ከራስ ሆቴል ጥቂት ክፍሎችን በመከራየት ስራው ጀመረ፡፡ በወቅቱ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር የነበሩትም እስራኤላዊው ሚስተር ዴቪድ ኤፍራተስ እንደነበሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። አሁን ላይ 50 ዓመት የሚላው ኢንስቲትዩቱ ምስረታውን ምክንያት በማድረግ "የመስተንግዶ ኢንዱስትሪ ፋናወጊ" በሚልመሪ ሃሳብ እያከበረ ይገኛል። በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም  ሚኒስቴር  ዴኤታ ወይዘሮ ቡዜና  አልቀድር  እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ፈጣን እድገት እንዲመጣ ትልቅ አስተዋፆ አበርክቷል። ለኢንዲስትሪው  ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን እንዲሁም የማማከር  አገልግሎት  በመስጠትም ላይ ይገኛል። በፍጥነት  እያደገ ያለውን  የቱሪዝም ዘርፍ ይበልጥ ለማጠናከር የስው ሃይል በብዛትና በጥራት  በማፈራት በኩል ተቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የአገልግሎት ስጪ ተቋማትም ብቃት ባለው የሰው ሃይል ተደራጅተው የአገልግሎት ጥራታቸውን በማሻሻል፤ በማዘመን ተወዳዳሪ ሆነው መገኘት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ኢዱስትሪው የሚጠይቀውን ባለሙያ በማፍራት  አገራዊ  ሃላፊነት ከመወጣት  አንጻር የሆቴልና ቱሪዝም  ስራ ማስልጠኛ ተቋማት  ጉልህ ድርሻ እንዳላቸውም አስረድተዋል። በቀጠይ በሆቴልና ቱሪዝም እድገቱ በሚፈለገው  ደረጃ ላይ ለመድረስ የባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ  ወሳኝ በመሆኑ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 50ኛ ዓመት ክብር በዓሉን  በውይይት፣ በስፖርታዊ ውድድሮች በመከበር ላይ ይገኛል
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም