ዩኒቨርሲቲው ብጥብጥ እንዲነሳ ባደረጉ 58 ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ዩኒቨርሲቲው ብጥብጥ እንዲነሳ ባደረጉ 58 ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ
71
ግንቦት 30/2011 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ የተቋሙ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲደናቀፍ ባደረጉ 58 ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ። የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ግንቦት 27 ቀን 2011ዓ.ም ባካሄደው አስቸካይ ስብሰባ ያሳለፈውን ውሳኔ ትናንት በውስጥ ማስታወቂያ ለተማሪዎች ይፋ አድርጓል። በዩኒቨርሲቲው ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማስተባበር፣ በመምራት እንዲሁም በግልና በቡድን በመሳተፍና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት በማድረስ እጅ ከፈንጅ የተያዙ 14 ወንድ እና ሁለት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው እንዲሰናበቱ ሴኔቱ ወስኗል። ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን በመያዝ በተማሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ላይ ጉዳት ለማድረስ የሞከሩ፣ ያደረሱና የተቋሙን ደንብ የጣሱ ሌሎች 12 ወንድ ተማሪዎችንም ለአንድ ዓመት ከትምህርታቸው ማገዱን ነው ያስታወቀው ። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሁከትና ብጥብጥ ተባባሪለ ነበሩ 30 ተማሪዎችም የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ሴኔቱ ባሳለፈው ውሳኔአ መልክቷል።