ሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር ማበልጸግ ስራዋን መቀጠሏ ተነገረ

91
ግንቦት30/2011 ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ማበልፀግ ስራዋን እያከናወነች እንደሆነ መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የቲንክ ታንክ ፕሮጀክት ተንታኞች  ገለጹ፡፡ የንግድ ሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሰሜን ኮሪያው ዩንግባዮን የኑውክሌር ሳይንቲፊክ ጥናት ማዕከሏን ወደ ስራ በማስገባት  የዩራኒየም ማበልፀጊያ ንጠረ ነገር በማልማት ላይ እንደሆነች ረቡዕ ዕለተ የወጡ የህትመት ውጤቶችን ለአብነት በመጥቅስ ዩ ፒ አይ ዘገባውን አጠናክሯል፡፡ ሪፖርቶች እደንደሚያሳዩት ከሆነ ተሸከርካሪዎች፣ ለግብዓትነት የሚጠቅሙ መሳሪያዎችና ሰራተኞች ማጓጓዣ መኪናና የመርከብ አገልግሎት የሚሰጡ፣ ጨምሮ  በርካታ ቁሳቁስ ወደ ኒውክሌር ማብላያ ጣቢያው መድረሳቸውን ዘገባው ያብራራል፡፡ ዩራኒየም በማመንጨት ሂደት ላይ ወሳኝ ሚና ካላቸው ነገሮች መካከል አንዱ የሆነው ፈሳሽ ናትሮጅንም ወደ ቦታው መድረሱን የሚያሳዩ ምስሎች አሉ ሲሉ ተንታኞች መፃፋቸውን ዘገባው ያሳያል፡፡ ሰሜን ኮሪያ የፍርስራሽ ቁሶችን በመጠቀም  የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በመገንባት  ላይ እንደሆነች ጭምር በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ዋሽንግተን እና ፖዮንግያንግ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸውን ተከትሎ የሰሜን ኮሪያዋን ሃገር ኒውክሌር ጦር መሳሪያ ማምረት መርሃግብር እንደትቀጥልበት ማድረጉን በመረጃው ሰፍሯል፡፡ ሰሜን ኮሪያ የምታመርተውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በመቀነስ የተጣለባትን አለም አቀፋዊ ማዕቀብ ለማስነሳት ብትፈልግም፤ አሜሪካ በበኩሏ ሰሜን ኮሪያ ሆይ ይህ ማዕቀብ እንዲነሳልሽ ከፈልግሽ መጀመሪያ እራስሽን ከኒውክኔር ማመረት ሂደት ሙሉ በሙሉ ነፃ አድርጊ ስትል ማስጠንቀቋን በማስታወስ ዘገባው አስፍሯል፡፡ አሜሪካና ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው የካቲት ወር ለሁለተኛ ጊዜ በቬትናሟ ዋና ከተማ ሃኖዌ የተካሄደው ውይይት ያለምንም ውጤት መጠናቀቁን በማስታውስ በዘገባው ተነስቷል፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም