የስኳር ኢንዱስትሪ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የምርምር ፎኖተ ካርታ ተዘጋጀ

64
አዳማ ግንቦት 30/2011 ኢትዮጵያን በስኳር ኢንዱስትሪ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የምርምር ፍኖተ ካርታ እየተዘጋጀ መሆኑን ስኳር ኮርፖሬሽን ገለጸ። ልማቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር የተዘጋጀው ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ለማዳበር የተዘጋጀ መድረክ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ አባል አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ እንደገለጹት በስኳር ኢንዱስትሪ አገሪቷን በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷል። ፍኖተ ካርታው የኢንዱስትሪውን አቅም በማጎልበትና በቆላማ አካባቢዎች አዳዲስና ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለማስፋፋትና አርብቶ አደሩን ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ መሆኑን አስረድተዋል። በአገርውስጥአቅርቦትናፍላጎትመካከልያለውንየአቅርቦትናፍላጎትእጥረትበዘላቂነትለማቃለልናምርቱየውጭምንዛሪምንጭለማድረግ  እንደሚያስችል ካይዳኪ  አመልክተዋል። በዘርፉየቴክኖሎጂናፈጠራ፣የሰውኃይልልማት በተለይምበውጭምንዛሪየሚገቡማሽኖችንናየመለዋወጫዕቃዎችንኢንዱስትሪውበሚፈልገውመጠንናበብዛትለማምረትያስችላልብለዋል። በተጨማሪም መድረኩ የስኳር ተረፈ ምርትን ጥቅም ላይ ለማዋል በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ድጋፍ እየተከናወኑ ፕሮጀክቶች ውጤታማ ለማድረግ ጭምር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል። የዘርፉን የምርምርና ልማት ሥራዎችን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር የ10 ዓመታት የሚቆይ ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን የገለጹት ደግሞ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃም አቶ ዋዮ ሮባ ናቸው። በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመደገፍ በዘርፉ የሚከናወኑ የፈጠራ ሥራዎችን በምርምር የሚበለጽግበት አቅም ግንባታና ስልጠና በሰው ኃይል ልማት ጭምር እንደሚከናወን ተናግረዋል። በዘርፉ በአገዳ ልማት የሚሳተፉ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ፣በኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የቴክኖሎጂና አዳዲስ አሰራሮች ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። በዘርፉ ያለውን መልካም አጋጣሚዎች፣ማነቆዎችና አማራጮችን በመዳሰስ የማስፈፀሚያ ስትራቴጂ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ ከምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎችና ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም