ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የሎዛ ማርያም ትምህርት ቤትን የግንባታ ሒደት ጎበኙ

175

ጎንደር ግንቦት 30/2011  ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጎንደር ከተማ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን የሎዛ ማርያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለጸው የትምህርት ቤቱ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 80 በመቶ የደረሰ ሲሆን በመጪው የትምህርት ዘመን አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ይሆናል።

በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ግንባታው   የተጀመረው ይሄው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአካባቢው ከሚመጡ ስድስት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ነው።

ቀዳማዊት እመቤት ከትምህርት ቤቱ ጉብኝት ጎን ለጎንም የችግኝ ተከላ አካሒደዋል።

በሌላም በኩል ቀዳማዊት እመቤት የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መዳረሻ በሆነው በደባርቅ ከተማ በ20 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው ይሄ ትምህርት ቤት በስድስት ብሎኮች 28 የመማሪያ ክፍሎችን የያዘ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም