በምዕራብ ሸዋ ዞን የ 63 ሜትር የሹኩቴ-ጩሉጤ አስፋልት መንገድ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

65

ግንቦት 30/2011በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሶስት ወረዳዎችን የሚያገናኝ 63 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ። 
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሶስት ወረዳዎችንየሚያገናኝ 63 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሰረተ ድንጋዩን የማስቀመጥ ስነስርዓቱ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢትዮጵያመንገዶችባለስልጣንዋናስራአስኪያጅ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት በተገኙበት የተከናወነ ነው።

የመንገዱ ግንባታ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚካሄድ ሲሆን ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን የተባለ አገር በቀል የስራ ተቋራጭ ግንባታውን ያካሄዳል።

 የመንገዱ ግንባታ  የግንደበረትና የአቡና ግንደበረት ወረዳን ህዝብ የረጅም ጊዜ የከፋ የመንገድ እጦት ችግር የሚፈታ ተብሎም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም