ዳኛ የተደበደበበት የመከላከያና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ ፍጻሜውን ሳያገኝ ቀርቷል

134
አዲስ አበባ ሚያዝያ 23/2010 በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ ዳኛ በተደበደበበት አሳፋሪ ተግባር መከላከያ ጨዋታውን ሁለት ለአንድ እየመራ ተቋርጧል። ትናንት የተደረገው ጨዋታ ለመከላከያ ከወራጅ ቀጠና ከሚገኙ ቡድኖች በነጥብ ለመራቅ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከወራጅ ቀጠና ስጋት ለመውጣት የሚያደርጉት በመሆኑ ለሁለቱ ቡድኖች በጣም ወሳኝ የሚባል ነው። በስታዲየሙ ብዙ ተመልካች ባልታደመበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጥላ ፎቅና በሚስማር ተራ የነበሩ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደጋፊዎች ቡድናቸውን ሲያበረታቱ የነበረ ሲሆን በአንጻሩ በጣት የሚቆጠሩ የመከላከያ ደጋፊዎች ለክለባቸው ድጋፍ ሲሰጡ ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱ ቡድኖች ኳስን ይዞ በመጫወትና በፈጣን የአንድ ሁለት ቅብብሎሽ ወደ ግብ ለመድረስ ሲያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ለተመልካቹ አዝናኝ የሚባል እንቅስቃሴ እንዲያይ አድርጎታል ማለት ይቻላል። በወልዋሎ በኩል ብርሃኑ አሻሞ፣ ዋለልኝ ገብሬና አፈወርቅ ሃይሉ በመከላከያ በኩል ዳዊት እስጢፋኖስ፣ በሀይሉ ግርማና ቴዎድሮስ ታፈሰ በመሐል ክፍሉ ብልጫ በመውሰድ ለመቆጣጠር ብርቱ ፍልሚያ ሲያደርጉ ታይቷል። መከላከያ በአጥቂ መስመር ላይ ፍጹም ገብረ ማርያምና ምንይሉ ወንድሙ የግብ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት ሲያደርግ የነበረ ሲሆን በአንጻሩ ወልዋሎ የማጥቃት እንቅስቃሴው በጋናውያኖቹ አዶንጎ ሬችሞንድና በአብዱርሃማን ፉሴይኒ የተመሰረተ ነበር። የወልዋሎ አጥቂዎች ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ የመከላከያ የተከላካይ ክፍል ተጫዋቾች ወደ ፊት በመሳብ ሲያደርጉ የነበረው ተግባር በተደጋጋሚ የወልዋሎ የአጥቂ መስመር ተጫዋቾችን ከጨዋታ ውጪ (ኦፍሳይድ) እንዲሆኑ አድርጓል። በስምንተኛው ደቂቃ ጋናዊው የወልዋሎ ተጫዋች ኦዶንጎ ሬችሞንድ ሞክሮ የመከላከያው ግብ ጠባቂ ይድነቃቸው ኪዳኔ ያወጣበት ኳስ በጨዋታው የመጀመሪያ ተጠቃሽ የሚባል የግብ ሙከራ ነበር። ሳሙኤል ታዬና ምንይሉ ወንድሙ ኢላማቸውን ያልጠበቁ ሙከራዎችን አድርገዋል። በ22ኛው ደቂቃ ወልዋሎዎች በአንድ ሁለት ቅብብል ያገኙትን ኳስ ጋናዊው ኦዶንጎ ሬችሞንድ ከመረብ ላይ በማሳረፍ ቡድኑን መሪ አድርጓል። 'ጎሉን ያስቆጠረው ኦዶንጎ ሬችሞንድ ኳሱን ሲቀበል ከጨዋታ ውጪ(ኦፍሳይድ) አቋቋም ላይ ነበር' በማለት የመከላከያ ተጫዋቾች ጎሉ መጽደቅ የለበትም በሚል ተቃውሟቸውን ለመሐል ዳኛውና ረዳት ዳኞች አቅርበዋል። መከላከያ ግብ ከተቆጠረበት በኋላ የማጥቃት እንቅስቃሴውን በማጠናከር ወደ ግብ ለመድረስ ጥረት አድርጓል። በ37ኛው ደቂቃ ሳሙኤል ታዬና ፍጹም ገብረማርያም በአንድ ሁለት ቅብብል ይዘው ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ይዘው የገቡትን ኳስ ቡርኪናፋሶያዊው ፕሪንስ ሰቨሪንሆ የመከላከያው ፍጹም ገብረ ማርያም ላይ በፈጸመው ጥፋት መከላከያ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቷል። የወልዋሎ አዲግራት የተወሰኑ ተጫዋቾች 'ፍጹም ቅጣት ምቱ ተገቢ አይደለም' በማለት ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሞገቱ ሲሆን የቡድኑ የአሰልጣኝ ቡድን ውሳኔውን ተገቢ አይደለም በአራተኛው ዳኛ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ ታይቷል። የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ምንይሉ ወንድሙ የወልዋሎውን በረኛ በረከት ተሰማ ባለበት በማቆም ግቡን በማስቆጠር መከላከያን አቻ ማድረግ ችሏል። የአቻነቱ ግብ ከተተቆጠረ በኋላ በሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ሽኩቻ የበዘባት ጨዋታ የታየ ሲሆን ተጫዋቾች ዱላ ቀረሽ የቃላት መለዋወጥ ሲያደርጉ ለመመልከት ተችሏል። ፌዴራል ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቁን የሚያበስረውን ፊሽካ ካሰሙ በኋላ የወልዋሎ አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማርያምና ሌሎች የአሰልጣኝ ቡድኑ አባላት ዳኞቹ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበረ ሲሆን ለአራተኛውም ዳኛ ክስ አስመዝግበዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የአሰልጣኝነት ቡድን ዳኛው የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎችን በመቃወም በተደጋጋሚ ጊዜ ከተቀያሪ ወንበር በመነሳት ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር። ከእረፍት መልስ መከላከያ በሀይሉ ግርማን አስወጥቶ አማኑኤል ተሾመን ቀይሮ ሲያስገባ ወልዋሎ ብርሃኑ አሻሞን አስወጥቶ አሳሪ አልመሐዲን ወደ ሜዳ አስገብቷል። ቅያሪዎቹ ሁለቱ ቡድኖች በአማካይ ክፍል ያለውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የተደረጉ ናቸው ማለት ይቻላል። ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ ጨዋታው ማራኪና በረከት ያሉ የግብ አጋጣሚዎች በሁለቱ ቡድኖች የተፈጠሩበት ነበር። መከላከያ በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ብልጫ የወሰደ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች በሳሙኤል ታዬና ምንይሉ ወንድሙ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችሏል። በ63ኛው ደቂቃ የመከላከያው የቀኝ መስመር ተጫዋች ምንተስኖት ከበደ በግሩም ሁኔታ ያሻገረውን ኳስ ሳሙኤል ታዬ በግንባሩ ሞክሮ የወልዋሎው ግብ ጠባቂ በረከት ተሰማ ጨርፎት የግቡን ቋሚ የመለሰው ሲሆን ቋሚውን ለትሞ የተመለሰውን ኳስ ፍጹም ገብረ ማርያም ቢሞክራትም በግቡ ጎን ታካ ወጥታለች። የሁለቱ ቡድኖች እንቅስቃሴ በዚሁ ሁኔታ እየቀጠለ ባለበት ሰአት የኤሌትሪክ ሃይል በመጥፋቱ ምክንያት በ70ኛው ደቂቃ ላይ የስታዲየሙ ፓውዛዎች የጠፉ ሲሆን በዚህም ምክንያት ጨዋታው የቆየው እስከ 73ኛው ደቂቃ ነበር። ፌዴራል ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ ጨዋታው እንዲቋረጥ ያደርጉ ሲሆን የስታዲየሙ ፓውዛ እስኪመጣ 18 ደቂዎችን ፈጅቷል። ጨዋታው ከ18 ደቂቃዎች በኋላ ከተጀመረ በኋላ ከመቋረጡ በፊት የነበረውን እንቅስቃሴ ማየት ያልተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ጨዋታው በመሐል ክፍል ላይ ብቻ ያመዘነ ነበር። መከላከያ ሳሙኤል ሳሊሶን ወልዋሎ ማናዬ ፋንቱን ቀይሮ ወደ ሜዳ በማስገባት የማጥቃት እንቅስቃሴውን ለማጠናከር ጥረት አድርገዋል። በ84ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር የተሻገረውን ፍጹም ገብማርያም ኳሷን በመጭረፍ ጎል አስቆጥሯል። የወልዋሎ ግብ ጠባቂ በረከት ተሰማ ኳሱ ከእጁ ላይ አምልጦት ከመስመር በማለፉ ዳኛው ጎሉን አጽድቀውታል። ሆኖም የወልዋሎው ግብ ጠባቂ በረከት አማረ ኳሱን በእጁ በመያዙ ግቡ አልተቆጠረም በማለት ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን ሌሎች የወልዋሎ ተጨዋቾችም ፌዴራል ዳኛ እያሱ ፈንቴን የከበቡት ሲሆን የመሐል ዳኛው የማዕዘን መምቻ ባንዲራውን ዘንግ ነቅሎ ራሱን በመከላከል በሽሽት ወደ መሮጫው ትራክ አምርቷል። በዚህ ክስተት ምክንያት ግርግር የተፈጠረ ሲሆን ከተቀያሪ ወንበር በመነሳት ወደ ዳኛው የሮጠው የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቡድን መሪ አቶ ማሩ ገብረፃዲቅ ዳኛውን መሬት ላይ በመጣል በቡጢ ሲማቱ ታይቷል። የቡድን መሪው የፈጸሙት ተግባር እጅግ በጣም አሳፋሪ ሲሆን ከስፖርታዊ ጨዋነት መጉደል ባለፈ ሰብአዊነት የጎደለው ተግባር ነው። ግቡን ያስቆጠረው ፍጹም ገብረማርያም በወልዋሎ ተጫዋቾች ተመቷል። ዳኛውን የደበደቡት የወልዋሎ የቡድን መሪ ከክለቡ አመራሮች ጠንካራ የሚባል ተቃውሞ የደረሰባቸው ሲሆን በዕለቱ የነበሩ የጸጥታ ሃይሎች የቡድን መሪውን ማሩ ገብረፃዲቅን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምርተዋል። የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የአሰልጣኝነት ቡድን በአጠቃላይ በጨዋታው ሲያሳዩት የነበረው ተግባር ፍጹም ስነ ምግባር የጎደለው ነው። ከዚህም በኋላ ዳኛውና የጨዋታው አመራሮች ወደ መልበሻ ክፍል ገብተው ከተወያዩ በኋላ ጨዋታው 84ኛው ደቂቃ ላይ እንዲቋረጥ ወስነዋል። በቀጣይ የጨዋታው ኮሚሽነር ጨዋታውን አስመልክቶ የሚያቀርበው ሪፖርት የሚጠበቅ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ በመመስረት የስነ መግባር ኮሚቴ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በክልል የተጀመረው ዳኛን የመደብደብ አሳፋሪ ተግባር ትናንትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ተመልክተናል። ሚያዚያ 3 ቀን 2010 ዓ.ም በ19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሼህ ሙሃመድ አላሙዲ ስታዲየም ወልዲያ ፋሲል ከተማን ባስተናገደበት ጨዋታ ተመሳሳይ ተግባር ተፈጽሟል። በፋሲል ተጫዋች ላይ በተፈጸመ ጥፋት የ90ኛ ደቂቃ ፍፁም ቅጣት ምት ከድር ኸይረዲን ወደ ግብነት ቀይሮት ፋሲል ሁለት ለአንድ መምራት ችሎ ነበር። ሆኖም ከግቡ በኋላ የተወሰኑ የወልዲያ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባት የመሀል ዳኛውን ለሚ ንጉሴና ረዳት ዳኛውን ሙስጠፋ መኪ በመደብደብ ጉዳት ማድረሳቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የተፈጸመውን ተግባር ተከትሎ የኢትዮዽያ ዳኞችና ታዛቢዎች ሙያ ማህበር ባወጣው የአቋም መግለጫ 'የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞችን መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ይገባዋል' ብሎ ነበር። ሚያዚያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም በ19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሶዶ ስታዲየም ወላይታ ድቻና ሃዋሳ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተመሳሳይ ተግባር ፈጽሟል። ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ዳኛው ላይ ከፍተኛ ተቃውሞን በማሰማት ድንጋይ በሚወረውሩበት ወቅት ጉዳት አድርሰዋል። ይህንን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ሁኔታውን ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት ከአንድ ሰአትት በላይ ወስዶ እና ጭሱ በስታድየሙ በነበሩ ተመልካቾች ላይ ጉዳት አድርሶ አመሻሽ ላይ መረጋጋቱ ይታወሳል። እነዚህ ክስተቶች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ለዳኞች የሚያደርጉትን ጥበቃ ጥያቄ ውስጥ የሚከትና የሚፈጸሙት ተግባራት የዳኞችን ህይወት አደጋ ውስጥ የሚከቱ ናቸው። የሚመለከተው አካልም አስፈላጊውን ጥበቃ ለዳኞች ማድረግ ይገባዋል። በ21ኛ ሳምንት ፕሪሚየር ሊግ ትናንት ክልል ላይ በተደረገ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ በአማኑኤል ጎበና፣ ጸጋዬ አበራና በእንዳለ ከበደ የፍጹም ቅጣት ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስን ሶስት ለባዶ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ጅማ አባ ጅፋር በ39 ነጥብ ሲመራ መቀሌ ከተማ በ35 ነጥብ ሁለተኛ ነው። ደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ አዳማ ከተማና ፋሲል ከተማ በተመሳሳይ 33 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከሶስት እስከ ሰባት ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት ናይጄሪያዊው የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች ኦኪኪ አፎላቢ በ14 ጎል ሲመራ፣ የደደቢቱ ጌታነህ ከበደና የአዳማ ከተማው ዳዋ ሁቴሳ በተመሳሳይ ዘጠኝ ግቦች ይከተላሉ። አዲስ አበባ ሚያዝያ 23/2010 በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ ዳኛ በተደበደበበት አሳፋሪ ተግባር መከላከያ ጨዋታውን ሁለት ለአንድ እየመራ ተቋርጧል። ትናንት የተደረገው ጨዋታ ለመከላከያ ከወራጅ ቀጠና ከሚገኙ ቡድኖች በነጥብ ለመራቅ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከወራጅ ቀጠና ስጋት ለመውጣት የሚያደርጉት በመሆኑ ለሁለቱ ቡድኖች በጣም ወሳኝ የሚባል ነው። በስታዲየሙ ብዙ ተመልካች ባልታደመበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጥላ ፎቅና በሚስማር ተራ የነበሩ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደጋፊዎች ቡድናቸውን ሲያበረታቱ የነበረ ሲሆን በአንጻሩ በጣት የሚቆጠሩ የመከላከያ ደጋፊዎች ለክለባቸው ድጋፍ ሲሰጡ ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱ ቡድኖች ኳስን ይዞ በመጫወትና በፈጣን የአንድ ሁለት ቅብብሎሽ ወደ ግብ ለመድረስ ሲያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ለተመልካቹ አዝናኝ የሚባል እንቅስቃሴ እንዲያይ አድርጎታል ማለት ይቻላል። በወልዋሎ በኩል ብርሃኑ አሻሞ፣ ዋለልኝ ገብሬና አፈወርቅ ሃይሉ በመከላከያ በኩል ዳዊት እስጢፋኖስ፣ በሀይሉ ግርማና ቴዎድሮስ ታፈሰ በመሐል ክፍሉ ብልጫ በመውሰድ ለመቆጣጠር ብርቱ ፍልሚያ ሲያደርጉ ታይቷል። መከላከያ በአጥቂ መስመር ላይ ፍጹም ገብረ ማርያምና ምንይሉ ወንድሙ የግብ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት ሲያደርግ የነበረ ሲሆን በአንጻሩ ወልዋሎ የማጥቃት እንቅስቃሴው በጋናውያኖቹ አዶንጎ ሬችሞንድና በአብዱርሃማን ፉሴይኒ የተመሰረተ ነበር። የወልዋሎ አጥቂዎች ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ የመከላከያ የተከላካይ ክፍል ተጫዋቾች ወደ ፊት በመሳብ ሲያደርጉ የነበረው ተግባር በተደጋጋሚ የወልዋሎ የአጥቂ መስመር ተጫዋቾችን ከጨዋታ ውጪ (ኦፍሳይድ) እንዲሆኑ አድርጓል። በስምንተኛው ደቂቃ ጋናዊው የወልዋሎ ተጫዋች ኦዶንጎ ሬችሞንድ ሞክሮ የመከላከያው ግብ ጠባቂ ይድነቃቸው ኪዳኔ ያወጣበት ኳስ በጨዋታው የመጀመሪያ ተጠቃሽ የሚባል የግብ ሙከራ ነበር። ሳሙኤል ታዬና ምንይሉ ወንድሙ ኢላማቸውን ያልጠበቁ ሙከራዎችን አድርገዋል። በ22ኛው ደቂቃ ወልዋሎዎች በአንድ ሁለት ቅብብል ያገኙትን ኳስ ጋናዊው ኦዶንጎ ሬችሞንድ ከመረብ ላይ በማሳረፍ ቡድኑን መሪ አድርጓል። 'ጎሉን ያስቆጠረው ኦዶንጎ ሬችሞንድ ኳሱን ሲቀበል ከጨዋታ ውጪ(ኦፍሳይድ) አቋቋም ላይ ነበር' በማለት የመከላከያ ተጫዋቾች ጎሉ መጽደቅ የለበትም በሚል ተቃውሟቸውን ለመሐል ዳኛውና ረዳት ዳኞች አቅርበዋል። መከላከያ ግብ ከተቆጠረበት በኋላ የማጥቃት እንቅስቃሴውን በማጠናከር ወደ ግብ ለመድረስ ጥረት አድርጓል። በ37ኛው ደቂቃ ሳሙኤል ታዬና ፍጹም ገብረማርያም በአንድ ሁለት ቅብብል ይዘው ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ይዘው የገቡትን ኳስ ቡርኪናፋሶያዊው ፕሪንስ ሰቨሪንሆ የመከላከያው ፍጹም ገብረ ማርያም ላይ በፈጸመው ጥፋት መከላከያ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቷል። የወልዋሎ አዲግራት የተወሰኑ ተጫዋቾች 'ፍጹም ቅጣት ምቱ ተገቢ አይደለም' በማለት ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሞገቱ ሲሆን የቡድኑ የአሰልጣኝ ቡድን ውሳኔውን ተገቢ አይደለም በአራተኛው ዳኛ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ ታይቷል። የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ምንይሉ ወንድሙ የወልዋሎውን በረኛ በረከት ተሰማ ባለበት በማቆም ግቡን በማስቆጠር መከላከያን አቻ ማድረግ ችሏል። የአቻነቱ ግብ ከተተቆጠረ በኋላ በሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ሽኩቻ የበዘባት ጨዋታ የታየ ሲሆን ተጫዋቾች ዱላ ቀረሽ የቃላት መለዋወጥ ሲያደርጉ ለመመልከት ተችሏል። ፌዴራል ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቁን የሚያበስረውን ፊሽካ ካሰሙ በኋላ የወልዋሎ አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማርያምና ሌሎች የአሰልጣኝ ቡድኑ አባላት ዳኞቹ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበረ ሲሆን ለአራተኛውም ዳኛ ክስ አስመዝግበዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የአሰልጣኝነት ቡድን ዳኛው የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎችን በመቃወም በተደጋጋሚ ጊዜ ከተቀያሪ ወንበር በመነሳት ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር። ከእረፍት መልስ መከላከያ በሀይሉ ግርማን አስወጥቶ አማኑኤል ተሾመን ቀይሮ ሲያስገባ ወልዋሎ ብርሃኑ አሻሞን አስወጥቶ አሳሪ አልመሐዲን ወደ ሜዳ አስገብቷል። ቅያሪዎቹ ሁለቱ ቡድኖች በአማካይ ክፍል ያለውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የተደረጉ ናቸው ማለት ይቻላል። ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ ጨዋታው ማራኪና በረከት ያሉ የግብ አጋጣሚዎች በሁለቱ ቡድኖች የተፈጠሩበት ነበር። መከላከያ በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ብልጫ የወሰደ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች በሳሙኤል ታዬና ምንይሉ ወንድሙ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችሏል። በ63ኛው ደቂቃ የመከላከያው የቀኝ መስመር ተጫዋች ምንተስኖት ከበደ በግሩም ሁኔታ ያሻገረውን ኳስ ሳሙኤል ታዬ በግንባሩ ሞክሮ የወልዋሎው ግብ ጠባቂ በረከት ተሰማ ጨርፎት የግቡን ቋሚ የመለሰው ሲሆን ቋሚውን ለትሞ የተመለሰውን ኳስ ፍጹም ገብረ ማርያም ቢሞክራትም በግቡ ጎን ታካ ወጥታለች። የሁለቱ ቡድኖች እንቅስቃሴ በዚሁ ሁኔታ እየቀጠለ ባለበት ሰአት የኤሌትሪክ ሃይል በመጥፋቱ ምክንያት በ70ኛው ደቂቃ ላይ የስታዲየሙ ፓውዛዎች የጠፉ ሲሆን በዚህም ምክንያት ጨዋታው የቆየው እስከ 73ኛው ደቂቃ ነበር። ፌዴራል ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ ጨዋታው እንዲቋረጥ ያደርጉ ሲሆን የስታዲየሙ ፓውዛ እስኪመጣ 18 ደቂዎችን ፈጅቷል። ጨዋታው ከ18 ደቂቃዎች በኋላ ከተጀመረ በኋላ ከመቋረጡ በፊት የነበረውን እንቅስቃሴ ማየት ያልተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ጨዋታው በመሐል ክፍል ላይ ብቻ ያመዘነ ነበር። መከላከያ ሳሙኤል ሳሊሶን ወልዋሎ ማናዬ ፋንቱን ቀይሮ ወደ ሜዳ በማስገባት የማጥቃት እንቅስቃሴውን ለማጠናከር ጥረት አድርገዋል። በ84ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር የተሻገረውን ፍጹም ገብማርያም ኳሷን በመጭረፍ ጎል አስቆጥሯል። የወልዋሎ ግብ ጠባቂ በረከት ተሰማ ኳሱ ከእጁ ላይ አምልጦት ከመስመር በማለፉ ዳኛው ጎሉን አጽድቀውታል። ሆኖም የወልዋሎው ግብ ጠባቂ በረከት አማረ ኳሱን በእጁ በመያዙ ግቡ አልተቆጠረም በማለት ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን ሌሎች የወልዋሎ ተጨዋቾችም ፌዴራል ዳኛ እያሱ ፈንቴን የከበቡት ሲሆን የመሐል ዳኛው የማዕዘን መምቻ ባንዲራውን ዘንግ ነቅሎ ራሱን በመከላከል በሽሽት ወደ መሮጫው ትራክ አምርቷል። በዚህ ክስተት ምክንያት ግርግር የተፈጠረ ሲሆን ከተቀያሪ ወንበር በመነሳት ወደ ዳኛው የሮጠው የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቡድን መሪ አቶ ማሩ ገብረፃዲቅ ዳኛውን መሬት ላይ በመጣል በቡጢ ሲማቱ ታይቷል። የቡድን መሪው የፈጸሙት ተግባር እጅግ በጣም አሳፋሪ ሲሆን ከስፖርታዊ ጨዋነት መጉደል ባለፈ ሰብአዊነት የጎደለው ተግባር ነው። ግቡን ያስቆጠረው ፍጹም ገብረማርያም በወልዋሎ ተጫዋቾች ተመቷል። ዳኛውን የደበደቡት የወልዋሎ የቡድን መሪ ከክለቡ አመራሮች ጠንካራ የሚባል ተቃውሞ የደረሰባቸው ሲሆን በዕለቱ የነበሩ የጸጥታ ሃይሎች የቡድን መሪውን ማሩ ገብረፃዲቅን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምርተዋል። የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የአሰልጣኝነት ቡድን በአጠቃላይ በጨዋታው ሲያሳዩት የነበረው ተግባር ፍጹም ስነ ምግባር የጎደለው ነው። ከዚህም በኋላ ዳኛውና የጨዋታው አመራሮች ወደ መልበሻ ክፍል ገብተው ከተወያዩ በኋላ ጨዋታው 84ኛው ደቂቃ ላይ እንዲቋረጥ ወስነዋል። በቀጣይ የጨዋታው ኮሚሽነር ጨዋታውን አስመልክቶ የሚያቀርበው ሪፖርት የሚጠበቅ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ በመመስረት የስነ መግባር ኮሚቴ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በክልል የተጀመረው ዳኛን የመደብደብ አሳፋሪ ተግባር ትናንትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ተመልክተናል። ሚያዚያ 3 ቀን 2010 ዓ.ም በ19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሼህ ሙሃመድ አላሙዲ ስታዲየም ወልዲያ ፋሲል ከተማን ባስተናገደበት ጨዋታ ተመሳሳይ ተግባር ተፈጽሟል። በፋሲል ተጫዋች ላይ በተፈጸመ ጥፋት የ90ኛ ደቂቃ ፍፁም ቅጣት ምት ከድር ኸይረዲን ወደ ግብነት ቀይሮት ፋሲል ሁለት ለአንድ መምራት ችሎ ነበር። ሆኖም ከግቡ በኋላ የተወሰኑ የወልዲያ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባት የመሀል ዳኛውን ለሚ ንጉሴና ረዳት ዳኛውን ሙስጠፋ መኪ በመደብደብ ጉዳት ማድረሳቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የተፈጸመውን ተግባር ተከትሎ የኢትዮዽያ ዳኞችና ታዛቢዎች ሙያ ማህበር ባወጣው የአቋም መግለጫ 'የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞችን መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ይገባዋል' ብሎ ነበር። ሚያዚያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም በ19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሶዶ ስታዲየም ወላይታ ድቻና ሃዋሳ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተመሳሳይ ተግባር ፈጽሟል። ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ዳኛው ላይ ከፍተኛ ተቃውሞን በማሰማት ድንጋይ በሚወረውሩበት ወቅት ጉዳት አድርሰዋል። ይህንን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ሁኔታውን ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት ከአንድ ሰአትት በላይ ወስዶ እና ጭሱ በስታድየሙ በነበሩ ተመልካቾች ላይ ጉዳት አድርሶ አመሻሽ ላይ መረጋጋቱ ይታወሳል። እነዚህ ክስተቶች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ለዳኞች የሚያደርጉትን ጥበቃ ጥያቄ ውስጥ የሚከትና የሚፈጸሙት ተግባራት የዳኞችን ህይወት አደጋ ውስጥ የሚከቱ ናቸው። የሚመለከተው አካልም አስፈላጊውን ጥበቃ ለዳኞች ማድረግ ይገባዋል። በ21ኛ ሳምንት ፕሪሚየር ሊግ ትናንት ክልል ላይ በተደረገ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ በአማኑኤል ጎበና፣ ጸጋዬ አበራና በእንዳለ ከበደ የፍጹም ቅጣት ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስን ሶስት ለባዶ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ጅማ አባ ጅፋር በ39 ነጥብ ሲመራ መቀሌ ከተማ በ35 ነጥብ ሁለተኛ ነው። ደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ አዳማ ከተማና ፋሲል ከተማ በተመሳሳይ 33 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከሶስት እስከ ሰባት ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት ናይጄሪያዊው የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች ኦኪኪ አፎላቢ በ14 ጎል ሲመራ፣ የደደቢቱ ጌታነህ ከበደና የአዳማ ከተማው ዳዋ ሁቴሳ በተመሳሳይ ዘጠኝ ግቦች ይከተላሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም